እባካችሁ ተከታትላችሁ እርዱት (S-43) የተባለውን ቅጽ እንዴት ልንጠቀምበት ይገባል?
ይህን ቅጽ መሙላት የሚኖርባችሁ ከክልላችሁ ውጪ የሚኖር ወይም የውጭ አገር ቋንቋ ተናጋሪ የሆነ ፍላጎት ያለው ሰው በምታገኙበት ጊዜ ነው። ከዚህ በፊት የውጭ አገር ቋንቋ ተናጋሪ የሆነ ሰው ስናገኝ ፍላጎት ቢያሳይም ባያሳይም ይህን ቅጽ እንሞላ ነበር፤ አንሁን ግን በዚህ ቅጽ የምንጠቀመው ያገኘነው ሰው ፍላጎት ካሳየ ብቻ ነው። ግለሰቡ መስማት የተሳነው ከሆነ ግን ሁኔታው ከዚህ የተለየ ይሆናል። መስማት የተሳነው ሰው ካጋጠመን ፍላጎት አሳየም አላሳየ S-43 የተባለውን ቅጽ መሙላት ይኖርብናል።
ቅጹን ከሞላን በኋላ ምን ማድረግ ይኖርብናል? ለጉባኤያችን ጸሐፊ መስጠት አለብን። ጸሐፊው ቅጹ ወደ የትኛው ጉባኤ መላክ እንዳለበት የሚያውቅ ከሆነ በቀጥታ ለዚያ ጉባኤ ሽማግሌዎች ይልከዋል፤ ከዚያም ሽማግሌዎቹ ግለሰቡን ተከታትሎ ለመርዳት ዝግጅት ያደርጋሉ። ጸሐፊው ለየትኛው ጉባኤ ማስተላለፍ እንዳለበት ካላወቀ ግን ቅጹን ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ይልከዋል።
ፍላጎት ያሳየው ሰው በእናንተ ክልል ውስጥ የሚኖር የውጭ አገር ቋንቋ ተናጋሪ ከሆነ በውጭ አገር ቋንቋ ከሚመራ ጉባኤ አንድ አስፋፊ መጥቶ እስኪያነጋግረው ድረስ ፍላጎቱን ለማሳደግ ተመላልሳችሁ ልትጠይቁት ትችላላችሁ።—የኅዳር 2009 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4ን ተመልከት