የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“ሁሉም ሰው፣ በመላው ዓለም ሰላም ቢኖር ደስ ይለዋል። ግን አሁንም ቢሆን ጦርነት አለ። ዓለም አቀፍ ሰላም የሕልም እንጀራ ሆኖ የቀረው ለምን ይመስልዎታል?” ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። መጠበቂያ ግንብ መጽሔቱን ስጠውና በመጨረሻ ገጽ ላይ ያለውን ዓምድ አሳየው። ከዚያም በመጀመሪያው ጥያቄ ሥር ባለው ሐሳብ ላይ እና በዚያ ውስጥ ከተጠቀሱት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ በአንዱ ላይ ተወያዩ። መጽሔቶቹን ካበረከትክለት በኋላ በሚቀጥለው ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
ማሳሰቢያ፦ ይህ የመግቢያ ሐሳብ በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ በሚደረገው የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ ላይ መቅረብ ይኖርበታል።
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
“በሁሉም አካባቢዎች ስለተለመደ አንድ ችግር ከሰዎች ጋር አጠር ያለ ውይይት እያደረግን ነበር። አብዛኞቹ ሰዎች የጭፍን ጥላቻ ሰለባ ሆነው ያውቃሉ። ከጭፍን ጥላቻ የጸዳ ዓለም ይመጣል ብለው አስበው ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም የሐዋርያት ሥራ 10:34ን አንብብ።] አምላክ ሰዎችን እንዴት እንደሚመለከት ልብ ይበሉ። ይህ መጽሔት አምላክ ጭፍን ጥላቻን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚያስወግደው እንዴት እንደሆነ ይናገራል።”
ንቁ! ሰኔ
“ስለ አንድ ጉዳይ ምን አመለካከት እንዳለዎት ብናውቅ ደስ ይለናል። ሁሉም ሰው የተሻለ ሕይወት ማግኘት ይፈልጋል። ታዲያ ብዙ ቁሳዊ ነገሮችን በመግዛት ይህን ፍላጎታችንን ማርካት የምንችል ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ኢየሱስ የተናገረውን ትልቅ ቁም ነገር የያዘ ሐሳብ ላሳይዎት። [ሉቃስ 12:15ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ለቁሳዊ ነገሮች ሚዛናዊ አመለካከት እንዲኖረን የሚረዳን ከመሆኑም በላይ ወጪያችንን ለመቆጣጠር ምን ማድረግ እንደምንችል ይጠቁመናል።”