የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ተመልሶ የሚመጣበትን ጊዜ ይጠባበቃሉ። ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ፣ ምን ቢያደርግ ደስ ይልዎታል?” ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። የታኅሣሥ 1ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና በመጨረሻ ገጽ ላይ ያለውን ዓምድ አሳየው። ከዚያም በመጀመሪያው ጥያቄ ሥር ባለው ሐሳብ እና በዚያ ውስጥ ከተጠቀሱት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ በአንዱ ላይ ተወያዩ። መጽሔቶቹን ካበረከትክለት በኋላ በሚቀጥለው ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 1
“አሁን አሁን ሰዎች ሕይወታቸው በሩጫ የተሞላ ስለሆነ ስለ አምላክ ማሰብ ተፈታታኝ ይሆንባቸዋል። እርስዎ በሕይወታችን ውስጥ ለአምላክ ቦታ መስጠት እንዳለብን ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ኢየሱስ ዝነኛ በሆነ የተራራ ስብከቱ ላይ፣ እውነተኛ ደስታ ለማግኘት መንፈሳዊ ነገሮች እንደሚያስፈልጉን ተናግሯል። [ማቴዎስ 5:3ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በሕይወታችን ውስጥ አምላክ ያስፈልገናል የምንልባቸውን ሦስት ምክንያቶች ይጠቅሳል።”
ንቁ! ታኅሣሥ
“በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት የምንሰማቸው ወይም የምናነብባቸው ነገሮች በብዙዎቻችን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ የታወቀ ነው። በመገናኛ ብዙኃን የሚቀርበው ዜና ትክክልና እውነተኛ እንደሆነ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ የምንሰማውን ነገር ከማመናችን በፊት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርብን ይናገራል። [ኢዮብ 12:11ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የምንሰማቸውንና የምናነብባቸውን ነገሮች እውነተኝነት ለመፈተን የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮች ይዟል።”