የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/14 ገጽ 4
  • የአቀራረብ ናሙናዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአቀራረብ ናሙናዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • የናሙና አቀራረቦች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • ሥራ ሲታክትህ መፍትሔው ምንድን ነው?
    ንቁ!—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
km 8/14 ገጽ 4

የአቀራረብ ናሙናዎች

በመስከረም ወር የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ

“ብዙ ሰዎች በመላእክት ያምናሉ። እርስዎስ በመላእክት ያምናሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መላእክት መንፈሳዊ ፍጥረታት ስለሆኑ ከፍተኛ ኃይል አላቸው፤ ግን እኛን ሊረዱን የሚችሉ ይመስልዎታል? መላእክት በዛሬው ጊዜ ሰዎችን የሚረዱት እንዴት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።” ከዚያም የመስከረም 1 መጠበቂያ ግንብ የመጨረሻ ገጽ ላይ ያለውን የመጀመሪያ ጥያቄ አሳየው፤ በጥያቄው ሥር ባለው ሐሳብ እና በአንቀጹ ላይ ካሉት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ በአንዱ ላይ ተወያዩ። መጽሔቶቹን ካበረከትክለት በኋላ በሚቀጥለው ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።

መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1

“ሰዎች ምድርን እንዳትጠገን አድርገው እያበላሿት እንደሆነ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] የሰው ልጆች ያደረሱትን ጉዳት ማስተካከል ባይችሉም አምላክ ግን ይህን የማድረግ ችሎታውም ሆነ ፍላጎቱ እንዳለው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ይህ ማረጋገጫ በ⁠መዝሙር 65:9 ላይ ይገኛል። [ጥቅሱን አንብብ።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም አምላክ ወደፊት ምድራችንን የሚንከባከባት እንዴት እንደሆነና የሰው ልጆች በዚህ ጊዜ ምን በረከቶች እንደሚያገኙ ያብራራል። መጽሔቱን ብሰጥዎት ደስ ይለኛል።”

ንቁ! መስከረም

“ብዙዎች አሠሪዎቻቸው ከመጠን በላይ እንዲሠሩ እንደሚጠብቁባቸው ይሰማቸዋል፤ በዚህም የተነሳ ውጥረት ውስጥ ይገባሉ። ከባድ የሥራ ጫና በሰውነታችንም ሆነ በስሜታችን ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ። አንድ ሰው ከሥራ ጋር በተያያዘ ሚዛኑን መጠበቅ እንዲችል ምን የሚረዳው ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ትኩረት የሚስብ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ላንብብልዎት። [መክብብ 4:6⁠ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ቅድሚያ ልንሰጣቸው የሚገቡ ነገሮችን ለይተን ለማወቅ እንዲሁም በሥራ ጫና የሚመጣ የጤና ቀውስ እንዳያጋጥመን ለማድረግ የሚረዱ አራት መንገዶችን ያብራራል።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ