ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ምሳሌ 7-11
“ልባችሁን . . . አታዘንብሉ”
ይሖዋ ያወጣቸው መሥፈርቶች ጥበቃ ያስገኙልናል። ከእነዚህ መሥፈርቶች ጥቅም ማግኘት ከፈለግን ግን በልባችን ልንይዛቸው ይገባል። (ምሳሌ 7:3) አንድ የይሖዋ አገልጋይ ልቡ ወደ መጥፎ ነገር እንዲያዘነብል ከፈቀደ ለሰይጣን መሠሪ ዘዴዎች ይጋለጣል። ምሳሌ ምዕራፍ 7 ልቡ እንዲያታልለው ስለፈቀደ አንድ ወጣት ይገልጻል። ይህ ወጣት ከሠራቸው ስህተቶች ምን ትምህርት እናገኛለን?
ሰይጣን እኛን ከይሖዋ ለማራቅ አምስቱን የስሜት ሕዋሳታችንን በመጠቀም መጥፎ ነገሮችን እንድንሠራ ሊገፋፋን ይሞክራል
ጥበብና ማስተዋል መጥፎ ድርጊት መፈጸም የሚያመጣውን አስከፊ ውጤት እንድንገነዘብና ከመንፈሳዊ አደጋ እንድንርቅ ይረዱናል