ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 2 ቆሮንቶስ 11-13
“ሥጋዬን የሚወጋ እሾህ”
እሾህ የሚለው ቃል፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በምሳሌያዊ መንገድ ብዙ ጊዜ ተሠርቶበታል። ቃሉ፣ ጉዳት የሚያስከትሉና አስቸጋሪ ሰዎችን ወይም ችግር የሚፈጥሩ ነገሮችን ሊያመለክት ይችላል። (ዘኁ 33:55፤ ምሳሌ 22:5፤ ሕዝ 28:24) ጳውሎስ “ሥጋዬን የሚወጋ እሾህ” ያለው፣ የሐዋርያነት ሥልጣኑን ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆኑ ብሎም ሥራውን የሚነቅፉ ሐሰተኛ ሐዋርያትንና ሌሎች ሰዎችን ለማመልከት ሊሆን ይችላል። ጳውሎስ “ሥጋዬን የሚወጋ እሾህ” በማለት የተናገረው ስለ ሌላ ነገርም ሊሆን እንደሚችል ከዚህ በታች ያሉት ጥቅሶች የሚጠቁሙት እንዴት ነው?
አንተስ ‘ሥጋህን የሚወጋው እሾህ’ ምንድን ነው?
ሁኔታውን በጽናት ለመቋቋም በይሖዋ እንደምትታመን ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?