ክርስቲያናዊ ሕይወት
ከእነዚህ ወንድሞች ምን ትምህርት ታገኛለህ?
በቅርቡ የተሾምክ የጉባኤ አገልጋይ ወይም ሽማግሌ ነህ? ሌሎች ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች የሌላቸው ችሎታ፣ ተሰጥኦ ወይም የትምህርት ደረጃ ይኖርህ ይሆናል። ይሁን እንጂ ከእነዚህ ወንድሞችም ሆነ በዕድሜ መግፋት ወይም በጤና ችግር የተነሳ አሊያም ቤተሰባቸውን ለመንከባከብ ሲሉ በኃላፊነት ቦታ ማገልገላቸውን ካቆሙ ሌሎች ታማኝ ወንዶች ብዙ ትምህርት መቅሰም ትችላለህ።
ተሞክሮ ያካበቱትን አክብሯቸው የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
1. ወንድም ሪቻርድስ ለወንድም ቤሎ አክብሮት ያሳየው እንዴት ነው?
2. ቤን ምን ስህተት ሠርቷል? ለምንስ?
3. ቤን ከኤልሳዕ ምሳሌ ምን ተምሯል?
4. ወንድሞችም ሆኑ እህቶች ተሞክሮ ላላቸው የእምነት ባልንጀሮቻቸው አክብሮት ማሳየትና ከእነሱ መማር የሚችሉት እንዴት ነው?