ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፀአት 29–30
ለይሖዋ የሚሰጥ መዋጮ
የማደሪያ ድንኳኑ በተገነባበት ወቅት ሀብታም ድሃ ሳይል ሁሉም ሰዎች መዋጮ በማድረግ የይሖዋን አምልኮ የመደገፍ መብት አግኝተው ነበር። እኛስ ለይሖዋ መዋጮ መስጠት የምንችለው እንዴት ነው? አንዱ መንገድ ለጉባኤና ለስብሰባ አዳራሾች፣ ለርቀት የትርጉም ቢሮዎች፣ ለቤቴል ሕንፃዎች እንዲሁም ለይሖዋ አምልኮ ለተወሰኑ ሌሎች ሕንፃዎች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ነው።
የገንዘብ መዋጮ በማድረግ እውነተኛውን አምልኮ መደገፍን በተመለከተ ከሚከተሉት ጥቅሶች ምን ትምህርት እናገኛለን?