የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb21 ጥር ገጽ 3
  • ወላጆች፣ ለልጆቻችሁ እውቀት አስጨብጧቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ወላጆች፣ ለልጆቻችሁ እውቀት አስጨብጧቸው
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የቤተሰብህን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?—ክፍል 2
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ወላጆች ልጆቻችሁን ከአደጋ ጠብቁ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • ወላጆች፣ ልጆቻችሁ ይሖዋን እንዲወዱ እርዷቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • ልጆቻችን ውድ ስጦታ ናቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
mwb21 ጥር ገጽ 3
ወላጆች ልጆቻቸውን እንዴት ራሳቸውን መጠበቅ እንደሚችሉ ሲያስተምሯቸው፤ ልጆቹ እንዴት ‘ተው!’ ማለት እንደሚችሉ ሲለማመዱ።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ወላጆች፣ ለልጆቻችሁ እውቀት አስጨብጧቸው

የምንኖርበት ዓለም ጥሩውን መጥፎ፣ መጥፎውን ደግሞ ጥሩ አስመስሎ ያቀርባል። (ኢሳ 5:20) የሚያሳዝነው፣ አንዳንዶች ይሖዋ የሚጠላቸውን ነገሮች ያደርጋሉ፤ ይህም ተመሳሳይ ፆታ ባላቸው ሰዎች መካከል የሚፈጸምን ተገቢ ያልሆነ ምግባር ይጨምራል። ልጆቻችሁ በመጥፎ ድርጊት እንዲካፈሉ በትምህርት ቤት ባሉ እኩዮቻቸው ወይም በሌሎች ሰዎች ተጽዕኖ ይደረግባቸዋል። ታዲያ ልጆቻችሁ እንደነዚህ ያሉ ፈተናዎችን እንዲቋቋሙ ልታዘጋጇቸው የምትችሉት እንዴት ነው?

ለልጆቻችሁ ስለ ይሖዋ መሥፈርቶች እውቀት አስጨብጧቸው። (ዘሌ 18:3) መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፆታ ሥነ ምግባር ምን እንደሚል ደረጃ በደረጃና ዕድሜያቸውን ባገናዘበ መልኩ አስተምሯቸው። (ዘዳ 6:7) ራሳችሁን እንደሚከተለው በማለት ጠይቁ፦ ‘ተገቢ የሆኑ የፍቅር መግለጫዎች የትኞቹ እንደሆኑ፣ ልከኝነት የሚንጸባረቅበት አለባበስ አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ እንዲሁም ሌሎች ባሉበት ማድረግ ስለሌለባቸው ነገሮች ልጆቼን አሠልጥኛቸዋለሁ? ልጆቼ አንድ ሰው የብልግና ምስሎችንና ጽሑፎችን (ፖርኖግራፊ) ሊያሳያቸው ቢሞክር ወይም በይሖዋ ፊት ትክክል ያልሆነ ነገር እንዲያደርጉ ቢጠይቃቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያውቃሉ?’ ልጆቻችሁ ተገቢውን እውቀት ማግኘታቸው ከብዙ ችግር ይጠብቃቸዋል። (ምሳሌ 27:12፤ መክ 7:12) ይሖዋ የሰጣችሁ ውድ ውርሻ የሆኑትን ልጆቻችሁን በማስተማር፣ ለእነሱ ያላችሁን ፍቅር ማሳየት ትችላላችሁ።—መዝ 127:3

እስከ መጨረሻው የሚጸና ቤት ገንቡ—ልጆቻችሁን ‘ከክፉ ነገር’ ጠብቁ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ‘እስከ መጨረሻው የሚጸና ቤት ገንቡ—ልጆቻችሁን ‘ከክፉ ነገር’ ጠብቁ’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። አንዲት እናትና ልጇ ‘ልጆቻችሁን ከጥቃት ጠብቁ’ የተባለውን ቪዲዮ ሲያዩ።

    አንዳንዶች ልጆቻቸውን ስለ ፆታ ጉዳዮች ማስተማር የሚከብዳቸው ለምንድን ነው?

  • ‘እስከ መጨረሻው የሚጸና ቤት ገንቡ—ልጆቻችሁን ‘ከክፉ ነገር’ ጠብቁ’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ወላጆች ‘ከታላቁ አስተማሪ ተማር’ በተባለው መጽሐፍና በሌሎች ጽሑፎች ላይ ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ሲወያዩ።

    ወላጆች ልጆቻቸውን “በይሖዋ ተግሣጽና ምክር” ማሠልጠን ያለባቸው ለምንድን ነው?—ኤፌ 6:4

  • ‘እስከ መጨረሻው የሚጸና ቤት ገንቡ—ልጆቻችሁን ‘ከክፉ ነገር’ ጠብቁ’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። በአፍሪካ የሚኖሩ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ጥቅሶችን እያነበቡ ሲወያዩ።

    እውቀት ጥበቃ ያስገኛል

    የይሖዋ ድርጅት ወላጆች ልጆቻቸውን ስለ ፆታ ጉዳዮች እንዲያስተምሩ ለመርዳት ምን ዝግጅት አድርጓል?—w19.05 12 ሣጥን

  • ልጆቻችሁ ከባድ ችግር ሳያጋጥማቸው በፊት አዘውትራችሁ ልታዋሯቸው የሚገባው ለምንድን ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ