ክርስቲያናዊ ሕይወት
“ስጡ”
ኢየሱስ ልግስና ወደ ሌሎች የሚጋባ ባሕርይ እንደሆነ ጠቁሟል። (ሉቃስ 6:38) አዘውትራችሁ የምትሰጡ ከሆነ ወንድሞቻችሁና እህቶቻችሁም ደግና ለጋስ ለመሆን ይነሳሳሉ።
በደስታ መስጠት የአምልኳችን ክፍል ነው። ይሖዋ ለተቸገሩ የእምነት ባልንጀሮቻቸው ልግስና እና ሞገስ የሚያሳዩ ክርስቲያኖችን በትኩረት ይመለከታል፤ ብድራት እንደሚከፍላቸውም ቃል ገብቷል።—ምሳሌ 19:17
ለስጦታችሁ እናመሰግናለን የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
የምታደርጉት መዋጮ ወንድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን ለመደገፍ የሚውለው እንዴት ነው?
የስጦታው መጠን ትልቅም ይሁን ትንሽ፣ ልግስና ማሳየታችንን መቀጠል ያለብን ለምንድን ነው?—በተጨማሪም “የአንዱ ትርፍ የሌላውን ጉድለት ይሸፍናል” የሚለውን jw.org ላይ የሚገኝ ርዕስ ተመልከት።