የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w24 ሚያዝያ ገጽ 31
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ታማኝነት በማሳየት ኢታይን ምሰሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • “ፈቃድህን እንድፈጽም አስተምረኝ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • በሕይወታችሁ የሚያጋጥሟችሁን ለውጦች ለመቋቋም በአምላክ መንፈስ ታመኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ይሖዋ በጥንት ዘመናት ሕዝቦቹን ‘ታድጓል’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
w24 ሚያዝያ ገጽ 31

ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዳዊት ሠራዊት ውስጥ እስራኤላውያን ያልሆኑ ሰዎች ያገለገሉት ለምንድን ነው?

በዳዊት ሠራዊት ውስጥ ካገለገሉት እስራኤላዊ ያልሆኑ ወታደሮች መካከል አሞናዊው ጼሌቅ፣ ሂታዊው ኦርዮ እና ሞዓባዊው ይትማ ይገኙበታል።a (1 ዜና 11:39, 41, 46) ከእነዚህም በተጨማሪ የዳዊት ሠራዊት ‘ከሪታውያንን፣ ጴሌታውያንን እና ጌታውያንን’ ያካተተ ነበር። (2 ሳሙ. 15:18) ከሪታውያን እና ጴሌታውያን ከፍልስጤማውያን ጋር የቅርብ ዝምድና እንዳላቸው ይገመታል። (ሕዝ. 25:16) ጌታውያን ደግሞ የፍልስጤም ከተማ የሆነችው የጌት ሰዎች ናቸው።—ኢያሱ 13:2, 3፤ 1 ሳሙ. 6:17, 18

ዳዊት እስራኤላዊ ያልሆኑ ሰዎችን ወደ ሠራዊቱ ያስገባው ለምንድን ነው? ለእሱ፣ ከዚህም በላይ ደግሞ ለይሖዋ ታማኞች እንደሚሆኑ እርግጠኛ ስለነበር ነው። ለምሳሌ ከሪታውያንን እና ጴሌታውያንን በተመለከተ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት እንዲህ ይላል፦ “ዳዊት በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ በነበረበት ጊዜም እንኳ ታማኞች ሆነውለት ነበር።” እንዴት? “የእስራኤል ሰዎች በሙሉ” ንጉሥ ዳዊትን ትተው “ሳባ የሚባል አንድ አስቸጋሪ ሰው” በተከተሉበት ወቅት ከሪታውያን እና ጴሌታውያን ለዳዊት ታማኞች በመሆን የሳባን ዓመፅ አክሽፈውለታል። (2 ሳሙ. 20:1, 2, 7) በሌላ ወቅት ደግሞ የንጉሥ ዳዊት ልጅ አዶንያስ ንግሥናውን በጉልበት ለመንጠቅ ሞክሮ ነበር። በዚህም ጊዜ ቢሆን ከሪታውያን እና ጴሌታውያን ለዳዊት ታማኞች በመሆን ይሖዋ የመረጠው ሰለሞን ንግሥናውን እንዲረከብ ረድተውታል።—1 ነገ. 1:24-27, 38, 39

ለዳዊት አስደናቂ ታማኝነት ካሳዩት እስራኤላዊ ያልሆኑ ሰዎች መካከል ጌታዊው ኢታይ ይገኝበታል። የዳዊት ልጅ አቢሴሎም ባመፀና የእስራኤላውያን ልብ በንጉሡ ላይ እንዲሸፍት ባደረገ ጊዜ ኢታይና 600 ወታደሮቹ ንጉሥ ዳዊትን ደግፈዋል። መጀመሪያ ላይ ዳዊት፣ ኢታይ የባዕድ አገር ሰው ስለሆነ በዚህ ውጊያ ላይ መሰለፍ እንደማይጠበቅበት ነግሮት ነበር። ነገር ግን ኢታይ “ሕያው በሆነው በይሖዋና ሕያው በሆነው በጌታዬ በንጉሡ እምላለሁ፣ በሕይወት ብኖርም ሆነ ብሞት ጌታዬ ንጉሡ በሚገኝበት በማንኛውም ቦታ ሁሉ እኔ አገልጋይህም በዚያ እሆናለሁ!” በማለት መለሰ።—2 ሳሙ. 15:6, 18-21

ኢታይ እና ንጉሥ ዳዊት በደስታ ሲነጋገሩ።

ኢታይ ይሖዋ ለሾመው ለንጉሥ ዳዊት ታማኝ ነበር

ምንም እንኳ ከሪታውያን፣ ጴሌታውያን እና ጌታውያን የባዕድ አገር ሰዎች ቢሆኑም ይሖዋ እውነተኛ አምላክ እንደሆነና ዳዊት በይሖዋ የተሾመ ንጉሥ እንደሆነ ተገንዝበው ነበር። መቼም ዳዊት እንደዚህ ያሉ ታማኝ ሰዎች በዙሪያው በመኖራቸው አመስጋኝ እንደሚሆን አያጠራጥርም።

a በዘዳግም 23:3-6 ላይ የሚገኘው የአምላክ ሕግ አሞናውያን እና ሞዓባውያን ወደ እስራኤላውያን ጉባኤ እንዳይገቡ ይከለክላል። ነገር ግን ሕጉ የሚከለክለው የብሔሩ ሙሉ ሕጋዊ አባል መሆንን እንጂ ከአምላክ ሕዝብ ጋር መቀላቀልን ወይም በመካከላቸው መኖርን አይመስልም። ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል (እንግሊዝኛ) ጥራዝ 1 ገጽ 95⁠ን ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ