የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w25 ታኅሣሥ ገጽ 31
  • ታስታውሳለህ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህ?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ታስታውሳለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ክፍል 1
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
w25 ታኅሣሥ ገጽ 31

ታስታውሳለህ?

በዚህ ዓመት የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በደንብ አንብበሃቸዋል? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

ለይሖዋ ክብር ለመስጠት የሚያነሳሳን ምንድን ነው?

ለይሖዋ ክብር የምንሰጠው አክብሮት ስለሚገባውና ከልባችን ስለምንወደው ነው። በተጨማሪም ለይሖዋ ክብር የምንሰጠው ሌሎች ስለ እሱ እንዲያውቁ ስለምንፈልግ ነው።—w25.01 ገጽ 3

አንድ ሰው ቅር ካሰኘን ይቅር ባይ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?

ስሜታችንን ችላ ልንለው አይገባም፤ ሆኖም ያደረብንን ቁጣና ቂም ስንተው ልባችን በምሬት እንዳይጎዳ እንጠብቀዋለን።—w25.02 ገጽ 15-16

ደቀ መዝሙሩ ማርቆስ ለወጣት ወንድሞች ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው ለምንድን ነው?

ማርቆስ ሌሎችን ለማገልገል ፈቃደኛ ነበር። ባጋጠመው ሁኔታ የተነሳ አዝኖና ስሜቱ ተጎድቶ ሊሆን ቢችልም ተስፋ አልቆረጠም። ከጳውሎስና ከሌሎች የጎለመሱ ወንድሞች ጋር መቀራረቡን ቀጥሏል።—w25.04 ገጽ 27

ኢየሱስ “ስምህን አሳውቄአቸዋለሁ” ብሎ ሲጸልይ ምን ማለቱ ነበር? (ዮሐንስ 17:26)

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የአምላክ ስም ይሖዋ መሆኑን ቀድሞውንም ቢሆን ያውቃሉ። ሆኖም ኢየሱስ ስለ ይሖዋ ማንነት ይኸውም ስለ ዓላማዎቹ፣ ስለ ሥራዎቹና ስለ ባሕርያቱ ይበልጥ እንዲያውቁ ረድቷቸዋል።—w25.05 ገጽ 20-21

ልካችንን የምናውቅ ከሆነ ምን አምነን እንቀበላለን?

የማናውቃቸው ነገሮች እንዳሉ አምነን እንቀበላለን። ለምሳሌ መጨረሻው መቼ እንደሚመጣ እንዲሁም ይሖዋ በዚያ ወቅት ምን ዓይነት እርምጃ እንደሚወስድ አናውቅም። ከዚህም ሌላ፣ ነገ ምን እንደሚሆን እንዲሁም ይሖዋ ምን ያህል እንደሚያውቀን አናውቅም።—w25.06 ገጽ 15-18

ከአንድ ጽሑፍ ወይም የሕዝብ ንግግር ጥቅም ለማግኘት ምን ሊረዳን ይችላል?

ራሳችንን እንዲህ ብለን ልንጠይቅ እንችላለን፦ ‘አድማጮች ይህን እውነት እንዲያምኑ ለመርዳት ምን ማስረጃ እየቀረበ ነው? ይህን እውነት ለሌላ ሰው ሳስተምር ልጠቀምበት የምችለው ውጤታማ ምሳሌ አለ? ይህ ርዕሰ ጉዳይ የማንን ትኩረት ሊስብ ይችላል?’—w25.07 ገጽ 19

ይሖዋ ዳዊትን የያዘበት መንገድ ስለ ይቅር ባይነቱ ምን ያስተምረናል?

ዳዊት ከባባድ ኃጢአቶችን የፈጸመ ቢሆንም ከልቡ ንስሐ ገብቷል፤ ይሖዋም ይቅር ብሎታል። (1 ነገ. 9:4, 5) አምላክ አንዴ ይቅር ካለ በኋላ ግለሰቡን ድጋሚ በዚያ ኃጢአት አይጠይቀውም።—w25.08 ገጽ 17

አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አንድን ነጥብ መረዳት ከከበደው ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

አንድን ነጥብ መጽሐፍ ቅዱስን ተጠቅማችሁ ለማስረዳት ጥረት ካደረጋችሁ በኋላም ጥናታችሁ ያንን ነጥብ መረዳት ከከበደው ነጥቡን አልፋችሁት ሌላ ጊዜ ልትመለሱበት ትችላላችሁ።—w25.09 ገጽ 24

መጽሐፍ ቅዱስ ኃጢአት “የማታለል ኃይል” እንዳለው ይናገራል። (ዕብ. 3:13) ይህ ምን ማለት ነው?

ኃጢአት መጥፎ ነገር እንድንፈጽም ይገፋፋናል። በተጨማሪም ይሖዋ የሚወደን መሆኑን ሁልጊዜ እንድንጠራጠር ሊያደርገን ይችላል።—w25.10 ገጽ 16

በግላችን የምናቀርበው ጸሎት ይበልጥ ትርጉም ያለው እንዲሆን የሚረዱን የትኞቹ ሦስት ነገሮች ናቸው?

(1) በይሖዋ ባሕርያት ላይ ማሰላሰል እንችላለን። (2) ያጋጠመንን ሁኔታ አስበን በጸሎታችን ላይ ልንጠቅሰው እንችላለን፤ ለምሳሌ ይቅር ልንለው የሚገባን ሰው ሊኖር ይችላል። (3) ረዘም ያለ ጸሎት ማቅረብ እንችላለን። እንዲህ ስናደርግ ውስጣዊ ሐሳባችንን መግለጽ ይበልጥ ቀላል ይሆንልናል።—w25.10 ገጽ 19-20

አረጋውያንን መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?

ለአረጋውያን ልንደውልላቸው ወይም ሄደን ልንጠይቃቸው እንችላለን። የሕክምና ቀጠሮ ሲኖራቸው አብረናቸው ልንሄድም እንችላለን። ወይም በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች አብረናቸው መካፈል እንችላለን።—w25.11 ገጽ 6-7

ይሖዋን የሚያስከብር የክርስቲያኖች ሠርግ የትኞቹን መሥፈርቶች ሊያሟላ ይገባል?

መንግሥት ያወጣቸውን ሕጎች አክብሩ። በሠርጉ ሥነ ሥርዓትም ሆነ በድግሱ ላይ የሚሰፍነው መንፈስ የአምላክ መንፈስ ፍሬ የሚንጸባረቅበት ሊሆን ይገባል። አለባበሳችሁ ልከኛ ይሁን፤ እንዲሁም ቅዱስ ጽሑፋዊ ካልሆኑ ልማዶች ራቁ። ለሠርጋችሁ በምትዘጋጁበት ጊዜ ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ አድርጉ።—w25.12 ገጽ 21-24

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ