የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwyp ርዕስ 102
  • ትምህርት ላቋርጥ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትምህርት ላቋርጥ?
  • የወጣቶች ጥያቄ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አንዳንዶች ትምህርት የሚያቋርጡበት ምክንያት
  • መዘዙን አስብ
  • የተሻለ አማራጭ
  • ትምህርቴን ማቋረጥ ይኖርብኛል?
    ንቁ!—2010
  • ትምህርቴን ባቋርጥ ይሻል ይሆን?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 1
  • ትምህርቴን ማቋረጥ ይኖርብኛልን?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች
  • ትምህርት ቢያስጠላኝስ?
    የወጣቶች ጥያቄ
ለተጨማሪ መረጃ
የወጣቶች ጥያቄ
ijwyp ርዕስ 102
በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኝ ልጅ በትምህርት ቤቱና በዚያ በሚማሩ ልጆች ተማሮ ሲሄድ።

የወጣቶች ጥያቄ

ትምህርት ላቋርጥ?

“ትምህርት ያስጠላኛል!” የሚል ስሜት ካለህ ለማቋረጥ ትፈተን ይሆናል። ይህ ርዕስ የተሻሉ አማራጮችን ለማግኘት ይረዳሃል።

  • አንዳንዶች ትምህርት የሚያቋርጡበት ምክንያት

  • መዘዙን አስብ

  • የተሻለ አማራጭ

  • እኩዮችህ ምን ይላሉ?

አንዳንዶች ትምህርት የሚያቋርጡበት ምክንያት

ባለሙያዎች ከሚጠቅሷቸው የተለመዱ ምክንያቶች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፦

  • ዝቅተኛ ውጤት። ‘የትምህርት ውጤቴ ከቀን ወደ ቀን እያሽቆለቆለ ነው።’

  • መሰላቸት። ‘ትምህርት ቤት የምማረው ነገር ለሕይወቴ የሚጠቅመኝ አይመስለኝም።’

  • የኢኮኖሚ ችግር። ‘ቤተሰቤን ለመደገፍ መሥራት አለብኝ።’

መዘዙን አስብ

መጽሐፍ ቅዱስ “ብልህ . . . አካሄዱን አንድ በአንድ ያጤናል” ይላል። (ምሳሌ 14:15) ነጥቡ ምንድን ነው? ትምህርት ለማቋረጥ እያሰብክ ከሆነ በመጀመሪያ ይህ ውሳኔ የሚያስከትልብህን መዘዝ አስብ።

ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦

  • ‘ትምህርት ማቋረጤ ወደፊት ሥራ ለመቀጠር ስሞክር ምን እንቅፋት ይፈጥርብኛል?’

    “ወደፊት ሥራ መያዝና ለቤተሰብህ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማቅረብ እንደሚያስፈልግህ አስታውስ። ትምህርት ካቋረጥክ ግን እንዲህ ማድረግ አስቸጋሪ ይሆንብሃል፤ ምክንያቱም አብዛኞቹ አሠሪዎች የሚቀጥሩት ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቀ ሰው ነው።”—ጁሊያ

  • ‘ትምህርት ማቋረጤ ችግሮችን የመጋፈጥ ችሎታዬን የሚነካው እንዴት ነው?’

    “ትምህርት ቤት ለወደፊቱ ሕይወት ያዘጋጅሃል። ወደፊት የምታገኛቸው ሰዎች፣ የሚያጋጥሙህ ፈተናዎችና የምትሠራው ሥራ አሁን በትምህርት ቤት እያጋጠመህ ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው።”—ዳንኤል

  • ‘ትምህርት ማቋረጤ ለሕይወት የሚያስፈልጉኝን መሠረታዊ ችሎታዎች እንዳላዳብር እንቅፋት አይፈጥርብኝም?’

    “የምትማረው ነገር ጥቅም አሁን ላይታይህ ይችላል። ግን 23 ዓመት ሞልቶህ ገቢህንና ወጪህን ማቀናነስ ሲኖርብህ ‘እንኳንም ሒሳብ ተማርኩ!’ ትላለህ።”—አና

የተሻለ አማራጭ

  • ምክር ጠይቅ። መጽሐፍ ቅዱስ “ብዙ አማካሪዎች ባሉበት . . . ስኬት ይገኛል” ይላል። (ምሳሌ 11:14) የትምህርት ውጤትህ እያሽቆለቆለ ከሆነ ወላጆችህ፣ አስተማሪህ፣ የተማሪዎች አማካሪ ወይም ሌላ የምታምነው አዋቂ ውጤትህን ለማሻሻል የሚረዳ ምክር እንዲሰጥህ ጠይቅ።

    “ትምህርት ከከበደህ አስተማሪህን አነጋግር። አንዳንዴ ችግሩ ከአስተማሪህ እንደሆነ ሊሰማህ ይችላል፤ አብዛኛውን ጊዜ ግን ምክር በመጠየቅ ብቻ ውጤትህን ማሻሻል ትችላለህ።”—ኤድዋርድ

  • አርቀህ አስብ። መጽሐፍ ቅዱስ “የአንድ ነገር ፍጻሜ ከጅማሬው ይሻላል” ይላል። (መክብብ 7:8) ትምህርት ስትጨርስ የሚኖርህ እውቀት ከተማርካቸው የትምህርት ዓይነቶች ጋር ብቻ የተያያዘ አይደለም፤ ለሕይወት አስፈላጊ የሆኑ ችሎታዎችም ይኖሩሃል።

    “አዋቂ ከሆንክ በኋላ የቤት ሥራ መሥራት ወይም ለፈተና ማጥናት ላይኖርብህ ይችላል። ሆኖም ትምህርት ቤት ሳለህ ውጥረትን የምትቋቋምበትን መንገድ መማርህ ወደፊት ከተመረቅክ በኋላ ለሚያጋጥሙህ ፈተናዎች ያዘጋጅሃል።”—ቬራ

    በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኝ ልጅ ጀልባው ወደቡ ጋ ከመድረሱ በፊት ሲወርድ። የክፍሉ ልጆችና አስተማሪው ከጀልባው እንዳይወርድ እያስጠነቀቁት ነው።

    ትምህርት ማቋረጥ ጀልባው ወደቡ ጋ ከመድረሱ በፊት እንደመውረድ ነው፤ ‘ምናለ እዚያው በቆየሁ ኖሮ’ ልትል ትችላለህ!

  • ያሉህን አማራጮች አስብ። መጽሐፍ ቅዱስ “ችኩሎች ሁሉ . . . ለድህነት ይዳረጋሉ” ይላል። (ምሳሌ 21:5) ያለህ ብቸኛ አማራጭ ትምህርት ማቋረጥ እንደሆነ ለመደምደም አትቸኩል። በኢንተርኔት እንዲሁም በምሽት ወይም በርቀት ፕሮግራም አማካኝነት ትምህርትህን መጨረስ ትችል ይሆናል።

    “ትምህርት ቤት በርትቶ መሥራትን፣ ችግሮችን መፍታትን እንዲሁም ከሌሎች ጋር አብሮ መሥራትን ያስተምርሃል። እነዚህ ነገሮች ለወደፊት ሕይወትህም ይጠቅሙሃል። ትምህርትህን ለመጨረስ የቻልከውን ሁሉ ጥረት ማድረግህ አያስቆጭም።”—ቤንጃሚን

ዋናው ነጥብ፦ ትምህርትህን ከጨረስክ አዋቂ ስትሆን የሚኖሩህን ኃላፊነቶች ለመወጣት የተሻለ ብቃት ይኖርሃል።

እኩዮችህ ምን ይላሉ?

አናቤል።

“ትምህርት ከጨረስክ ሥራ ለመቀጠር ማመልከቻ ስታስገባ ሥራውን የማግኘት አጋጣሚህ የተሻለ ይሆናል። ትምህርት መጨረስህ የጀመርከውን ነገር ማጠናቀቅ የምትችል ሰው እንደሆንክ የሚያሳይ ማስረጃ ነው። ትምህርት ማቋረጥ የሞኝነት ውሳኔ ነው።”—አናቤል

ኮል።

“ትምህርት መቀጠል ከባድ እንደሆነና ማቋረጡ የተሻለ አማራጭ እንደሆነ ሊሰማህ ይችላል። ሆኖም ሁልጊዜም ውጥረት የሚፈጥሩ ሁኔታዎችን መጋፈጥ ይኖርብሃል፤ ደግሞም አዋቂ ከሆንክ በኋላ ማንኛውንም ሁኔታ መወጣት የሚችል ሰው መሆን እንደምትፈልግ ግልጽ ነው። ትምህርት ለአዋቂነት ሕይወት ያዘጋጅሃል።”—ኮል

ብሪን።

“አዋቂ ስትሆን ውስብስብ የሆነ የሒሳብ ጥያቄ መመለስ ላያስፈልግህ ይችላል። ሆኖም ጊዜህን በጥበብ መጠቀም፣ የተጠየቅከውን ነገር በሚጠበቅብህ የጊዜ ገደብ ውስጥ ማድረስ እንዲሁም በጠዋት ከእንቅልፍህ መነሳት ያስፈልግሃል። የትምህርት ቤት ሕይወት እነዚህን ችሎታዎች ለማዳበር ሊረዳህ ይችላል።”—ብሪን

ክለሳ፦ ትምህርት ላቋርጥ?

  • መዘዙን አስብ። ትምህርት ማቋረጥህ ሥራ በማግኘት አጋጣሚህ፣ በወደፊት ግብህ አልፎ ተርፎም ችግሮችን በመቋቋም ችሎታህ ላይ ምን አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር አስብ።

  • ምክር ጠይቅ። ውጤትህ እያሽቆለቆለ ከሆነ ወላጅህን፣ አስተማሪህን፣ የተማሪዎችን አማካሪ ወይም የምታምነውን ሌላ ሰው ምክር ጠይቅ።

  • አርቀህ አስብ። የትምህርት ቤት ጥቅም ከምትማራቸው የትምህርት ዓይነቶች ጋር ብቻ የተያያዘ አይደለም። የትምህርት ቤት ሕይወት የጥናት ልማድ፣ የተጠየቅከውን ነገር በጊዜው የማድረስ ችሎታ እንዲሁም ኃላፊነት የመሸከም አቅም እንዲኖርህም ይረዳሃል።

  • ያሉህን አማራጮች አስብ። ያለህበት ሁኔታ ትምህርት ለማቋረጥ የሚያስገድድህ ከሆነ በኢንተርኔት እንዲሁም በምሽት ወይም በርቀት ፕሮግራም አማካኝነት ትምህርትህን መጨረስ ትችል እንደሆነ አስብ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ