የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwwd ርዕስ 13
  • የፖሜሎ ልጣጭ ያለው ግጭት የመቋቋም ችሎታ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የፖሜሎ ልጣጭ ያለው ግጭት የመቋቋም ችሎታ
  • ንድፍ አውጪ አለው?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የእባብ ቆዳ
    ንቁ!—2014
  • በአቍማዳ ውስጥ ያለ እንባ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የሻርክ ቆዳ
    ንድፍ አውጪ አለው?
  • ፀሐይ አፍቃሪዎች ለቆዳችሁ ጥንቃቄ አድርጉ!
    ንቁ!—1999
ለተጨማሪ መረጃ
ንድፍ አውጪ አለው?
ijwwd ርዕስ 13
ዛፍ ላይ ያለ የፖሜሎ ፍሬ።

ንድፍ አውጪ አለው?

የፖሜሎ ልጣጭ ያለው ግጭት የመቋቋም ችሎታ

ፖሜሎ በዛፍ ላይ የሚበቅል የብርቱካን ዝርያ የሆነ ጣፋጭ ፍሬ ነው። ይህ ፍሬ ከ10 ሜትር ከሚበልጥ ከፍታ ቢወድቅም ጉዳት አይደርስበትም። ፖሜሎ እንዲህ ያለ ግጭት የመቋቋም ችሎታ ሊኖረው የቻለው እንዴት ነው?

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ተመራማሪዎች ነጭ ቀለም ያለው የፖሜሎ ልጣጭ ውስጠኛ ክፍል እንደ ስፖንጅ ዓይነት ባሕርይ እንዳለው አስተውለዋል፤ በዚህ ክፍል ውስጥ ባሉት ሴሎች መካከል ክፍተት አለ። ወደሚበላው ክፍል እየተጠጋን ስንሄድ በሴሎቹ መካከል ያለው ክፍተት እየጨመረ ይሄዳል፤ ይህ ክፍተት በአየር ወይም በፈሳሽ የተሞላ ነው። ፍሬው ወድቆ ከመሬቱ ጋር ሲጋጭ ይህ ፈሳሽ እንደ ትራስ ይሆንለታል። የፖሜሎው ልጣጭ በመኮማተር የግጭቱን ኃይል ስለሚቋቋም ፍሬው አይፈርጥም።

ለሁለት የተቆረጠ የፖሜሎ ፍሬ፤ የስፖንጅ ባሕርይ ያለው ልጣጩ ይታያል። ጎላ የተደረገው ክፍል ሴሎቹና በመካከላቸው ያለው ክፍተት በአጉሊ መነፅር ሲታይ ምን እንደሚመስል ያሳያል።

ሳይንቲስቶች የፖሜሎ ልጣጭ ያለውን ንድፍ በመኮረጅ ከብረት የተሠራ ግጭትን መቋቋም የሚችል ፎም ያዘጋጁ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ሙከራ እያካሄዱበት ነው። ሳይንቲስቶች እንዲህ ያለው ንድፍ ለሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የጭንቅላት መከላከያ ለመሥራት፣ ለመኪኖች የግጭት መከላከያ ለማዘጋጀት እንዲሁም የጠፈር ጣቢያዎች በተወርዋሪ ኮከቦች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ለመከላከል እንደሚያስችል ያምናሉ።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? የፖሜሎ ልጣጭ ያለው ግጭት የመቋቋም ችሎታ በዝግመተ ለውጥ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ