የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 1/15 ገጽ 7
  • የማር እንጀራ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የማር እንጀራ
  • ንቁ!—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ማር—ንቦች ለሰዎች የሚሰጡት ገጸ-በረከት
    ንቁ!—2005
  • የንብ እርባታ “ጣፋጭ” ታሪክ
    ንቁ!—1998
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2015
  • ዓለም አቀፋዊ የጠፈር ጣቢያ፣ ምድርን የሚዞር ቤተ ሙከራ
    ንቁ!—1999
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2015
g 1/15 ገጽ 7
ንቦች በማር እንጀራ ላይ

ንድፍ አውጪ አለው?

የማር እንጀራ

ንቦች የማር እንጀራ የሚሠሩት በሆዳቸው የታችኛው ክፍል የሚገኙ እጢዎች የሚያመነጩትን ሰም ተጠቅመው ነው። የማር እንጀራ እጅግ የተራቀቀ የምሕንድስና ጥበብ እንደሆነ ይነገራል። ለምን?

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ አንድን ቦታ ስድስት ጎን ባለው ቅርጽ መከፋፈል በሦስት ማዕዘን፣ በካሬ ወይም በሌላ በማንኛውም ቅርጽ ከመከፋፈል በተሻለ በአነስተኛ የግንባታ ዕቃ ብዙ መያዝ የሚችል ክፍልፋይ ለመሥራት ያስችላል። የሒሳብ ሊቃውንት ይህን የተገነዘቡት ከበርካታ መቶ ዓመታት በፊት ቢሆንም ይህ የሆነበትን ምክንያት ግን ሙሉ በሙሉ አልተረዱም ነበር። በ1999 ፕሮፌሰር ቶማስ ሄልስ፣ የማር እንጀራ ቅርጽ ያለውን ብልጫ የሚያሳይ የሒሳብ ማስረጃ አቀረቡ፤ ይህንን ማስረጃ “የማር እንጀራ መላምት” ብለው ጠርተውታል። አንድን ቦታ ብዙ ጠንካራ ድጋፍ ሳያስፈልግ እኩል ቦታ ለመከፋፈል ከሁሉ የተሻለው መንገድ ባለስድስት እኩል ጎን ያለው ቅርጽ መጠቀም እንደሆነ ፕሮፌሰሩ አስረድተዋል።

ንቦች፣ ያላቸውን ቦታ ያለምንም ብክነት ለመጠቀም ቦታውን ባለስድስት ጎን በሆኑ ቅርጾች ይከፋፍሉታል፤ ይህም ጠንካራ ሆኖም ብዙ ክብደት የሌለው እንዲሁም በአነስተኛ ሰም ብዙ ማር የመያዝ አቅም ያለው የማር እንጀራ ለመሥራት ያስችላቸዋል። የማር እንጀራ “አስደናቂ ጥበብ የሚታይበት የግንባታ ንድፍ” መባሉ ምንም አያስደንቅም።

በዛሬው ጊዜ የሳይንስ ሊቃውንት የንቦችን የማር እንጀራ በመኮረጅ ጠንካራና አንድን ቦታ በተሻለ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችሉ ንድፎችን መሥራት ችለዋል። ለምሳሌ፣ የአውሮፕላን መሐንዲሶች የማር እንጀራን ንድፍ በመኮረጅ የተሠሩ ሰሌዳዎችን በመጠቀም ነዳጅ ቆጣቢ የሆኑ ጠንካራና ቀላል አውሮፕላኖችን ይሠራሉ።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? እጅግ ረቂቅ የሆነው የማር እንጀራ ቅርጽ በዝግመተ ለውጥ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጭ አለው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ