የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w13 5/1 ገጽ 15
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ ይቅር ይለኝ ይሆን?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ‘ይቅር ለማለት ዝግጁ’ የሆነ አምላክ
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
  • አምላክ ይቅር ሲለን በደላችንን አያስታውስም ማለት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ይሖዋ፣ “ይቅር ለማለት ዝግጁ” የሆነ አምላክ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
w13 5/1 ገጽ 15

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ኃጢአታችን ይቅር ሊባልልን ይችላል?

[በገጽ 15 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የአምላክን ሞገስ ማግኘት ከባድ ነገር አይደለም

ሁሉም ሰው ኃጢአተኛ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ከመጀመሪያው ሰው ከአዳም ኃጢአት የመሥራት ዝንባሌ ወርሰናል። በመሆኑም በኋላ ላይ የሚጸጽተንን መጥፎ ነገር የምንሠራበት ጊዜ አለ። የአምላክ ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል በመሞት ለኃጢአታችን ቤዛ ከፍሎልናል። ይህ ቤዛዊ መሥዋዕት የኃጢአት ይቅርታ ያስገኝልናል። ቤዛው የአምላክ ስጦታ ነው።—ሮም 3:23, 24⁠ን አንብብ።

አንዳንድ ሰዎች ከባድ ኃጢአት በመፈጸማቸው ምክንያት አምላክ እነሱን ይቅር ይላቸው እንደሆነ ይጠራጠራሉ። ደስ የሚለው ነገር የአምላክ ቃል “የልጁ የኢየሱስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” ይላል። (1 ዮሐንስ 1:7) ይሖዋ፣ ከባድ ኃጢአት ብንሠራ እንኳ ከልብ ንስሐ እስከገባን ድረስ ይቅር ሊለን ፈቃደኛ ነው።—ኢሳይያስ 1:18⁠ን አንብብ።

ኃጢአታችን ይቅር እንዲባልልን ምን ማድረግ አለብን?

ይሖዋ አምላክ ይቅር እንዲለን የምንፈልግ ከሆነ መንገዶቹን፣ ምክሩንና ከእኛ የሚፈልገውን ነገር ለማወቅ ስለ እሱ መማር ይኖርብናል። (ዮሐንስ 17:3) ይሖዋ የሚፈጽሙትን መጥፎ ድርጊት ትተው ንስሐ የሚገቡትንና ለመለወጥ ጥረት የሚያደርጉትን ሰዎች በደግነት ይቅር ይላቸዋል።—የሐዋርያት ሥራ 3:19⁠ን አንብብ።

የአምላክን ሞገስ ማግኘት ከባድ ነገር አይደለም። ይሖዋ ድክመታችንን ይረዳል። እሱ መሐሪና ደግ ነው። ታዲያ አምላክ መሐሪ መሆኑ እሱን እንዴት ማስደሰት እንደምትችል ለመማር አላነሳሳህም?—መዝሙር 103:13, 14⁠ን አንብብ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ