የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ll ክፍል 6 ገጽ 14-15
  • ከታላቁ የጥፋት ውኃ ምን እንማራለን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከታላቁ የጥፋት ውኃ ምን እንማራለን?
  • አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ክፍል 6
    አምላክን ስማ
  • ለዘመናችን ማስጠንቀቂያ የሚሆን ጥንት የተፈጸመ ታሪክ
    የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • ታላቁ የጥፋት ውኃ—አምላክን የሰሙት እነማን ነበሩ? ያልሰሙትስ?
    አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
  • ኖኅ የአምላክን ሞገስ እንዲያገኝ ያስቻለው ምንድን ነው? ይህ ጉዳይ ሊያሳስበን የሚገባው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
ለተጨማሪ መረጃ
አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
ll ክፍል 6 ገጽ 14-15

ክፍል 6

ከታላቁ የጥፋት ውኃ ምን እንማራለን?

አምላክ ክፉ ሰዎችን ያጠፋ ሲሆን ኖኅንና ቤተሰቡን ግን አድኗል። ዘፍጥረት 7:11, 12, 23

መርከቧ እየተንሳፈፈች፣ ክፉዎቹ ሰዎች ሲሰምጡ፣ ዓመፀኞቹ መላእክት ሥጋዊ አካላቸውን ትተው ሲሄዱ

አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ዝናብ ዘነበ፤ ምድሪቱም ሙሉ በሙሉ በውኃ ተሸፈነች። ክፉዎቹ ሰዎች በሙሉ ሞቱ።

ዓመፀኞቹ መላእክት ሥጋዊ አካላቸውን በመተው አጋንንት ሆኑ።

ኖኅ፣ ቤተሰቡና እንስሳቱ ከመርከቡ ሲወጡ፤ በሰማይ ላይ ቀስተ ደመና ይታያል

በመርከቡ ውስጥ የነበሩት ሰዎች በሕይወት ተረፉ። ኖኅና ቤተሰቡ ከጊዜ በኋላ የሞቱ ቢሆንም እንኳ አምላክ ለዘላለም እንዲኖሩ ከሞት ያስነሳቸዋል።

አምላክ አሁንም ክፉዎችን አጥፍቶ ጥሩ ሰዎችን ያድናል። ማቴዎስ 24:37-39

ሰይጣንና አጋንንቱ ሰዎችን ለማሳሳት የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ

ሰይጣንና አጋንንቱ ሰዎችን ማሳሳታቸውን ቀጥለዋል።

በኖኅ ዘመን እንደነበረው ሁሉ ዛሬም ብዙ ሰዎች የይሖዋን ፍቅራዊ መመሪያ አይቀበሉም። በቅርቡ ይሖዋ ክፉ ሰዎችን ሁሉ ያጠፋል።—2 ጴጥሮስ 2:5, 6

የይሖዋ ምሥክሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅመው ለአንድ ሰው ሲሰብኩ፤ አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ እያነበበ

እንደ ኖኅ ያሉ አንዳንድ ሰዎች አሉ። እነሱም አምላክን የሚሰሙ ሲሆን እሱ የሚለውን ያደርጋሉ፤ እነዚህ ሰዎች የይሖዋ ምሥክሮች ናቸው።

  • ወደ ሕይወት የሚወስደውን መንገድ ምረጥ።—ማቴዎስ 7:13, 14

  • ክፉዎች ይጠፋሉ፤ የዋሆች ግን ሰላም ያገኛሉ።—መዝሙር 37:10, 11

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ