የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መከራ ለደረሰባቸው ሰዎች የሚሆን መጽናኛ
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | ጥር 1
    • አምላክ ሰዎችን የፈጠረው ሥቃይና መከራ እንዲደርስባቸው አልነበረም። ከዚህ ይልቅ ለመጀመሪያዎቹ ሰብዓዊ ጥንዶች ለአዳምና ለሔዋን ምንም እንከን የሌለበት አእምሮና አካል ሰጥቷቸው፣ ለመኖሪያ የሚሆን የተዋበ የአትክልት ሥፍራ አዘጋጅቶላቸው እንዲሁም ዓላማ ያለውና እርካታ የሚያስገኝ ሥራ ሰጥቷቸው ነበር። (ዘፍጥረት 1:27, 28, 31፤ 2:8) ይሁን እንጂ ደስታቸው ዘላቂ መሆኑ የተመካው የአምላክን የበላይ ገዥነት እንዲሁም መልካሙንና ክፉውን ለመወሰን ያለውን መብት አምነው በመቀበላቸው ላይ ነበር። ይህን መለኮታዊ ሥልጣን የሚወክል ‘መልካምንና ክፉን የሚያስታውቅ’ የተባለ አንድ ዛፍ ነበር። (ዘፍጥረት 2:17) አዳምና ሔዋን ከዛፉ እንዳይበሉ አምላክ የሰጣቸውን መመሪያ በማክበር ለአምላክ መገዛታቸውን ማሳየት ይችሉ ነበር።a

  • መከራ ለደረሰባቸው ሰዎች የሚሆን መጽናኛ
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | ጥር 1
    • a ዘ ጀሩሳሌም ባይብል ዘፍጥረት 2:​17ን አስመልክቶ ባሰፈረው የግርጌ ማስታወሻ ላይ ‘መልካምንና ክፉን ማወቅ’ የሚለውን አባባል “ምን ነገር መልካም፣ ምን ነገር መጥፎ እንደሆነ የመወሰንና በዚያ መሠረት የመመራት ሥልጣን ማለትም የሰው ልጅ ፍጡር መሆኑን ለመቀበል አሻፈረኝ ብሎ ሙሉ በሙሉ በራስ ለመተዳደር ያደረገው ምርጫ” በማለት ይገልጸዋል። አክሎም “የመጀመሪያው ኃጢአት በአምላክ ሉዓላዊነት ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ነበር” ይላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ