-
ኢየሱስ በአምላክ ዓላማ ውስጥ የሚጫወተውን ልዩ ሚና ከፍ አድርጋችሁ ተመልከቱመጠበቂያ ግንብ—2008 | ታኅሣሥ 15
-
-
አስቀድሞ የተነገረለት “ዘር”
18. አዳም ኃጢአት ከሠራ በኋላ ምን ትንቢት ተነገረ? ይህን ትንቢት በተመለከተ ከጊዜ በኋላ ምን ነገር ታወቀ?
18 በኤደን ውስጥ የሰው ልጅ ሁሉንም ነገር ማለትም በአምላክ ፊት የነበረውን ንጹሕ አቋም፣ የዘላለም ሕይወትን፣ ደስታን እንዲሁም በገነት የመኖር አጋጣሚን ጨርሶ ያጣ ይመስል በነበረበት ወቅት ይሖዋ አምላክ አዳኝ እንደሚያስነሳ ትንቢት ተናገረ። ይህ አዳኝ ‘ዘር’ ተብሎ ተጠርቷል። (ዘፍ. 3:15) ባለፉት ዘመናት የተነገሩ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ጭብጥ ማንነቱ ባልተገለጸው በዚህ ዘር ላይ ያተኮረ ነበረ። ይህ ዘር ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ እንዲሁም ከንጉሥ ዳዊት የትውልድ ሐረግ እንደሚመጣ ተነግሮ ነበር።—ዘፍ. 21:12፤ 22:16-18፤ 28:14፤ 2 ሳሙ. 7:12-16
19, 20. (ሀ) ተስፋ የተደረገበት ዘር ማን ነው? (ለ) ተስፋ የተደረገበት ዘር ኢየሱስን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ይጨምራል ሊባል የሚችለው ለምንድን ነው?
19 ተስፋ የተደረገበት ይህ ዘር ማን ነበር? ገላትያ 3:16 ለዚህ ጥያቄ መልሱን ይሰጠናል። (ጥቅሱን አንብብ።) ይሁን እንጂ ሐዋርያው ጳውሎስ በዚሁ ምዕራፍ ላይ ቅቡዓን ክርስቲያኖችን እንዲህ ብሏቸው ነበር፦ “የክርስቶስ ከሆናችሁ፣ እናንተ የአብርሃም ዘር ናችሁ፤ እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።” (ገላ. 3:29) ቅቡዓን ክርስቲያኖችም የአብርሃም ዘር ተብለው ከተጠሩ ተስፋ የተደረገበት ዘር ክርስቶስ ነው ሊባል የሚችለው እንዴት ነው?
20 በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የአብርሃም ዝርያዎች እንደሆኑ የሚናገሩ ሲሆን እንዲያውም አንዳንዶች ነቢያት እንደሆኑ ይገልጻሉ። አንዳንድ ሃይማኖቶች፣ ነቢያቶቻቸው የአብርሃም ዘሮች እንደሆኑ የሚገልጹ ሲሆን ለዚህ ጉዳይ ትልቅ ቦታ ይሰጡታል። ይሁንና እነዚህ ሁሉ ሰዎች ተስፋ የተደረገው ዘር ናቸው? አይደሉም። ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ ተመርቶ እንደጻፈው ከአብርሃም ዝርያዎች መካከል ተስፋ የተደረገበት ዘር እንደሆኑ መናገር የሚችሉት ሁሉም አይደሉም። የሰው ልጆች የሚባረኩት በይስሐቅ ዘር ብቻ እንጂ በሌሎቹ የአብርሃም ልጆች በኩል አይደለም። (ዕብ. 11:18) አስቀድሞ የተነገረለት የዚህ ዘር ዋነኛ ክፍል አንድ ሰው ብቻ ሲሆን እሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ከአብርሃም ጀምሮ ያለው የትውልድ ሐረጉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቧል።b ከጊዜ በኋላ የአብርሃም ዘር ሁለተኛ ክፍል የሆኑት ሌሎች ሰዎች በሙሉ የዚህ ዘር ክፍል ሊሆኑ የቻሉት ‘የክርስቶስ በመሆናቸው’ ነው። በእርግጥም ኢየሱስ በዚህ ትንቢት አፈጻጸም ረገድ የተጫወተው ሚና ልዩ ነው።
-