-
ሁከት በነገሠበት በዚህ ዘመን ከአምላክ ጋር መሄድመጠበቂያ ግንብ—2005 | መስከረም 1
-
-
10, 11. (ሀ) አዳምና ሔዋን ካመጹ በኋላ ምግባረ ብልሹነት የተስፋፋው እንዴት ነው? (ለ) ሄኖክ ምን የሚል ትንቢታዊ መልእክት ይሰብክ ነበር? ምንስ ዓይነት ምላሽ እንዳጋጠመው እርግጠኛ መሆን እንችላለን?
10 ለምሳሌ ያህል አዳም ኃጢአት ከሠራ በኋላ ምግባረ ብልሹነት ምን ያህል በፍጥነት ተዛምቶ እንደነበር ተመልከት። የአዳም የበኩር ልጅ የሆነው ቃየን ወንድሙን አቤልን በመግደል የመጀመሪያው ነፍሰ ገዳይ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (ዘፍጥረት 4:8-10) አቤል በጭካኔ ከተገደለ በኋላ አዳምና ሔዋን ሌላ ልጅ ወልደው ስሙን ሴት አሉት። ስለ እርሱ እንዲህ የሚል እናነባለን:- “ለሴትም ደግሞ ወንድ ልጅ ተወለደለት፤ ስሙንም ሄኖስ አለው። በዚያም ዘመን ሰዎች የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ጀመሩ።” (ዘፍጥረት 4:25, 26) የሚያሳዝነው “የእግዚአብሔርን ስም መጥራት” የጀመሩት በክህደት መልክ ነበር።b ሄኖስ ከተወለደ በርካታ ዓመታት ካለፉ በኋላ የቃየን ዘር የሆነው ላሜህ ያቆሰለውን አንድ ወጣት እንደገደለ የሚገልጽ መዝሙር ለሁለት ሚስቶቹ ተቀኝቶላቸው ነበር። እንዲሁም “ቃየንን የሚገድል ሰባት ጊዜ ቅጣት ካገኘው፣ የላሜሕ ገዳይማ ሰባ ሰባት ጊዜ ቅጣት ያገኘዋል” በማለት አስጠንቅቆ ነበር።—ዘፍጥረት 4:10, 19, 23, 24
-
-
ሁከት በነገሠበት በዚህ ዘመን ከአምላክ ጋር መሄድመጠበቂያ ግንብ—2005 | መስከረም 1
-
-
b ይሖዋ ሄኖስ ከኖረበት ዘመን በፊት ከአዳም ጋር ተነጋግሮ ነበር። አቤልም ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት ለይሖዋ አቅርቧል። አልፎ ተርፎም አምላክ ቃየን በቅንዓት ተቆጥቶ ግድያ ከመፈጸሙ በፊት አነጋግሮታል። ስለዚህ ሰዎች “የእግዚአብሔርን ስም መጥራት” የጀመሩት ከንጹሕ አምልኮ ጋር በተያያዘ ሳይሆን ለየት ባለ መንገድ መሆን አለበት።
-