-
“ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር” ዳነመጠበቂያ ግንብ—2013 | ነሐሴ 1
-
-
ይሖዋ የመርከቧን በር ከዘጋ በኋላ በነበሩት 40 ቀናት ውስጥ የኖኅና የቤተሰቡ ሕይወት ምን ሊመስል እንደሚችል ለማሰብ ሞክር። ኃይለኛው ዶፍ ዝናብ መርከቡ ላይ መውረዱን ሲቀጥል ስምንቱም በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ማለትም እርስ በርስ እንደ መረዳዳት፣ ቤታቸውን እንደ ማስተካከልና በመርከቧ ውስጥ ለነበሩት እንስሳት የሚያስፈልጋቸውን እንደ ማቅረብ ባሉ ሥራዎች ተጠምደው ሊሆን እንደሚችል ግልጽ ነው። ይሁንና አንድ ቀን ያ ግዙፍ መርከብ በድንገት መናወጥ ጀመረ። ይህ የሆነው መርከቡ መንቀሳቀስ ስለጀመረ ነው! የውኃው ከፍታ እየጨመረ ሲሄድ መርከቧ ተንሳፈፈች፤ ከዚያም የውኃው መጠን ቀስ በቀስ ሲጨምር “መርከቧን ከምድር ወደ ላይ አነሣት።” (ዘፍጥረት 7:17) ሁሉን ቻይ አምላክ የሆነውን የይሖዋን ኃይል የሚያሳይ እንዴት ያለ አስደናቂ ትዕይንት ነው!
-
-
“ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር” ዳነመጠበቂያ ግንብ—2013 | ነሐሴ 1
-
-
‘ከውኃ ዳኑ’
መርከቧ በዚያ በሚናወጥ ውቅያኖስ ላይ በምትንሳፈፍበት ጊዜ የተሠራችበት እንጨት የሚያሰማው ሲጢጥ የሚልና የሚንቋቋ ድምፅ በውስጧ ለነበሩት ሰዎች መሰማቱ አይቀርም። ታዲያ በዚህ ጊዜ ኖኅ የሞገዱ ኃይለኛነት ወይም የመርከቧ ጥንካሬ አሳስቦት ይሆን? በፍጹም። በዘመናችን ያሉት ተጠራጣሪዎች እንዲህ ያለ ጭንቀት ይፈጠርባቸው ይሆናል፤ ኖኅ ግን እንዲህ ዓይነት ሰው አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ “ኖኅ . . . መርከብ የሠራው በእምነት” እንደሆነ ይናገራል። (ዕብራውያን 11:7) ለመሆኑ ኖኅ እምነት ያሳየው እንዴት ነበር? ይሖዋ ኖኅንና ከእሱ ጋር የነበሩትን ሁሉ ከዚያ የጥፋት ውኃ እንደሚያድናቸው ቃል ኪዳን ገብቶ ነበር። (ዘፍጥረት 6:18, 19) አጽናፈ ዓለምን፣ ምድርንና በላይዋ ላይ ያሉትን ሕይወት ያላቸው ነገሮች በሙሉ የፈጠረ አምላክ መርከቧ ምንም ጉዳት እንዳይደርስባት ሊጠብቃት ይችላል ብሎ ማሰብ ምክንያታዊ አይደለም? ምንም ጥያቄ የለውም! በእርግጥም ኖኅ፣ ይሖዋ ቃሉን እንደሚጠብቅ መተማመኑ ተገቢ ነው። ደግሞም እሱና ቤተሰቡ ‘ከውኃው ድነዋል።’—1 ጴጥሮስ 3:20
ዝናቡ ለ40 ቀንና ለ40 ሌሊት ከጣለ በኋላ በመጨረሻ አቆመ። ዝናቡ ያቆመው በዘመናችን አቆጣጠር መሠረት በ2370 ዓ.ዓ. ታኅሣሥ አካባቢ ነበር። የቤተሰቡ የመርከብ ላይ ሕይወት ግን ገና አላበቃም። ብዙ ፍጥረታትን የያዘችው ይህቺ መርከብ ተራሮች በሙሉ እስኪሸፈኑ ድረስ ምድርን ባጥለቀለቀው ባሕር ላይ ወዲያ ወዲህ ማለቷን ቀጥላለች። (ዘፍጥረት 7:19, 20) ኖኅ ሴምን፣ ካምንና ያፌትን በማስተባበር ለእንስሳቱ በሙሉ መኖ በማቅረብ እንዲሁም ንጽሕናቸውን በመጠበቅና ጤንነታቸውን በመንከባከብ አድካሚውን ሥራ ሲወጣ በዓይነ ሕሊናችን ሊታየን ይችላል። እርግጥ ነው፣ እነዚያን ሁሉ የዱር እንስሳት ታዛዥና ገራም በማድረግ በቀላሉ ወደ መርከቧ እንዲገቡ ያደረገ አምላክ ከመርከቧ እስኪወጡ ድረስ በዚሁ ሁኔታ እንዲቀጥሉ እንዳደረገላቸው ምንም ጥያቄ የለውም።a
-