-
‘አምላክን ምሰሉ’መጠበቂያ ግንብ—2008 | ጥቅምት 1
-
-
የአምላክ ቃል እውነተኛ ክርስቲያኖችን ‘እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች አምላክን ምሰሉ’ በማለት ይመክራቸዋል። (ኤፌሶን 5:1) እነዚህ ግሩም ቃላት አምላክ በአገልጋዮቹ እንደሚተማመን ያሳያሉ። እንዴት? ይሖዋ አምላክ ሰውን የፈጠረው በመልኩ ወይም በአምሳሉ ነው። (ዘፍጥረት 1:26, 27) በመሆኑም አምላክ ለሰው ልጆች የእሱን ባሕርያት የማንጸባረቅ ችሎታ ሰጥቷቸዋል።a ስለሆነም መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖችን ‘አምላክን የምትመስሉ ሁኑ’ ብሎ ሲመክራቸው፣ ይሖዋ እንደሚከተለው ያላቸው ያህል ነው፦ ‘በእናንተ እተማመናለሁ። ፍጹማን ባትሆኑም በተወሰነ ደረጃ እኔን መምሰል እንደምትችሉ እርግጠኛ ነኝ።’
-
-
‘አምላክን ምሰሉ’መጠበቂያ ግንብ—2008 | ጥቅምት 1
-
-
a ቈላስይስ 3:9, 10 በአምላክ መልክ መፈጠር ሲባል ባሕርያቱን ከማንጸባረቅ ጋር የተያያዘ መሆኑን ይጠቁማል። አምላክን ማስደሰት የሚፈልጉ ሰዎች ‘የፈጣሪውን [የአምላክን] መልክ እንዲመስል የሚታደሰውን አዲሱን ሰው’ እንዲለብሱ ተመክረዋል።
-