-
የአምላክ መንግሥት መግዛት ጀምሯልወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት
-
-
9 ይሖዋም በተመሳሳይ ስለ መንግሥቱ እውንነት ማረጋገጫ ሰጥቶናል። የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሆነው በዕብራውያን መጽሐፍ እንደተመለከተው የሕጉ የተለያዩ ክፍሎች ለመንግሥቱ ዝግጅት ጥላ ነበሩ። (ዕብራውያን 10:1) በተጨማሪም ምድራዊው የእስራኤል መንግሥት በአምላክ መንግሥት የሚኖረው ሁኔታ ምን እንደሚመስል ጭላንጭል ሰጥቷል። የእስራኤል መንግሥት ተራ መስተዳድር አልነበረም፤ ምክንያቱም ገዥዎቹ የተቀመጡት ‘በይሖዋ ዙፋን ላይ’ ነበር። (1 ዜና መዋዕል 29:23) ከዚህም በላይ “ሴሎ እስኪመጣ ድረስ በትረ መንግሥት ከይሁዳ እጅ አይወጣም፣ የአዛዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፤ የሕዝቦችም መታዘዝ ለእርሱ ይሆናል።” (ዘፍጥረት 49:10 አዓት)a አዎን፣ የአምላክ መንግሥት ዘላለማዊ ንጉሥ የሚሆነው ኢየሱስ የሚወለደው ከይሁዳ የትውልድ ሐረግ ነበር።— ሉቃስ 1:32, 33
-