-
ልክ እንደ አምላክ ለሕይወት ከፍተኛ ዋጋ ትሰጣለህ?‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
-
-
16. ውርጃ ትክክል እንዳልሆነ የሚያመለክተው የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓት የትኛው ነው? (በተጨማሪም የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት።)
16 በማህጸን ውስጥ ያለ ጽንስ እንኳ በአምላክ ዓይን ውድ ነው። በጥንት እስራኤል፣ አንድ ሰው ነፍሰ ጡር በሆነች ሴት ላይ ጉዳት ቢያደርስና በዚህም ምክንያት ሴቲቱ ወይም ጽንሱ ቢሞቱ፣ አምላክ ጉዳት ያደረሰውን ሰው እንደ ነፍሰ ገዳይ ስለሚቆጥረው “ሕይወት በሕይወት” እንዲከፍል ይደረግ ነበር።c (ዘፀአት 21:22, 23) በመሆኑም ይሖዋ፣ በየዓመቱ በውርጃ አማካኝነት ሕይወታቸው የሚቀጨውን ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሕፃናት ሲመለከት ምን እንደሚሰማው መገመት ትችላለህ፤ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ መሥዋዕት የሚደረጉት ከኃላፊነት ነፃ ለመሆንና በሥነ ምግባር ልቅ የሆነ ሕይወት ለመምራት ሲባል ነው።
-
-
ልክ እንደ አምላክ ለሕይወት ከፍተኛ ዋጋ ትሰጣለህ?‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
-
-
c የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት አዘጋጆች፣ ጥቅሱ በዕብራይስጥ የተጻፈበት መንገድ “በሴቲቱ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ብቻ የሚያመለክት ነው ለማለት አያስችልም” ይላሉ። በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ የጽንሱ ወይም የሽሉ ዕድሜ በይሖዋ ፍርድ ላይ የሚያመጣው ለውጥ ስለመኖሩ የሚናገረው ነገር እንደሌለ ልብ በል።
-