የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ንጹሕ አቋማችሁን ጠብቁ!
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019 | የካቲት
    • 3. (ሀ) ንጹሕ አቋም የሚለው አገላለጽ ከአምላክ አገልጋዮች ጋር በተያያዘ ምን ትርጉም አለው? (ለ) ለይሖዋ የምንሰጠው ነገር ጉድለት የሌለበት፣ እንከን የለሽ ወይም ሙሉ መሆን እንዳለበት እንድንረዳ የሚያግዘን የትኛው ምሳሌ ነው?

      3 ንጹሕ አቋም የሚለው አገላለጽ ከአምላክ አገልጋዮች ጋር በተያያዘ ሲሠራበት ይሖዋን እንደ እውን አካል በማየት እሱን በሙሉ ልብ መውደድንና ምንጊዜም ለእሱ ማደርን ያመለክታል፤ ይህም በምናደርጋቸው ውሳኔዎች ሁሉ የአምላክን ፈቃድ እንድናስቀድም ያነሳሳናል። እስቲ ይህ አገላለጽ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሠራባቸውን አንዳንድ መንገዶች እንመልከት። ንጹሕ አቋም የሚለው አገላለጽ ከሚያስተላልፋቸው መሠረታዊ ትርጉሞች መካከል አንዱ ጉድለት የሌለበት፣ እንከን የለሽ ወይም ሙሉ የሚል ነው። ለምሳሌ ያህል፣ እስራኤላውያን እንስሳትን ለይሖዋ መሥዋዕት አድርገው ያቀርቡ የነበረ ሲሆን ሕጉ እንስሳው እንከን የሌለበት እንዲሆን ያዛል።b (ዘሌ. 22:21, 22) የአምላክ ሕዝቦች እግሩ፣ ጆሮው ወይም ዓይኑ ላይ ችግር ያለበት አሊያም በበሽታ የተጠቃ እንስሳ እንዲያቀርቡ አይፈቀድላቸውም ነበር። ይሖዋ እንስሳው ጉድለት የሌለበት፣ እንከን የለሽ ወይም ሙሉ እንዲሆን ይፈልግ ነበር። (ሚል. 1:6-9) ይሖዋ የሚቀርብለት መሥዋዕት እንከን የለሽ ወይም ሙሉ እንዲሆን የሚፈልገው ለምን እንደሆነ መረዳት አይከብደንም። ለምሳሌ የበሰበሰ ፍራፍሬ፣ ገጾቹ ያልተሟሉ መጽሐፍ ወይም የሆነ ዕቃ የጎደለው መሣሪያ መግዛት አንፈልግም። የምንገዛው ነገር ጉድለት የሌለበት፣ እንከን የለሽ ወይም ሙሉ እንዲሆን እንፈልጋለን። ይሖዋም ለእሱ ከምናሳየው ፍቅርና ታማኝነት ጋር በተያያዘ ተመሳሳይ ነገር ይጠብቃል። ፍቅራችንና ታማኝነታችን ጉድለት የሌለበት፣ እንከን የለሽ ወይም ሙሉ መሆን ይኖርበታል።

  • ንጹሕ አቋማችሁን ጠብቁ!
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019 | የካቲት
    • b ከእንስሳት ጋር በተያያዘ “እንከን የሌለበት” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል ከሰው ልጆች ጋር በተያያዘ “ንጹሕ አቋም” ተብሎ ከተተረጎመው ቃል ጋር ተዛማጅነት አለው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ