-
ለመለኮታዊ ሥልጣን በታማኝነት ተገዙመጠበቂያ ግንብ—2002 | ነሐሴ 1
-
-
13. (ሀ) ዓመፀኞቹ በይሖዋ ፊት ዕጣን ለማቅረብ መሞከራቸው እንደ ድፍረት የሚቆጠረው ለምንድን ነው? (ለ) ይሖዋ በዓመፀኞቹ ላይ ምን እርምጃ ወሰደ?
13 በአምላክ ሕግ መሠረት ዕጣን እንዲያጥኑ የተፈቀደላቸው ካህናቱ ብቻ ነበሩ። ካህን ላልሆነ አንድ ሌዋዊ በይሖዋ ፊት ዕጣን ማቅረብ የሚለው ሐሳብ እነዚህን ዓመፀኞች ሊያስደነግጥና ወደ ልቦናቸው እንዲመለሱ ሊያደርጋቸው ይገባ ነበር። (ዘጸአት 30:7፤ ዘኁልቁ 4:16) ቆሬና ግብረ አበሮቹ ግን እንደዚህ ዓይነት ሰዎች አልነበሩም! በማግስቱ ቆሬ “ማኅበሩን ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእነርሱ [በሙሴና በአሮን] ላይ ሰበሰበ።” ዘገባው በመቀጠል እንዲህ ይላል:- “እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው:- ሁሉን በቅጽበት አጠፋቸው ዘንድ ከዚህ ማኅበር መካከል ፈቀቅ በሉ።” ሆኖም ሙሴና አሮን የሕዝቡን ሕይወት ለመታደግ ይሖዋን ተማጸኑ፤ እርሱም እርምጃ ከመውሰድ ተመለሰ። ቆሬንና ግብረ አበሮቹን ግን “እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጥታ ያጥኑ የነበሩትን ሁለት መቶ አምሳ ሰዎች በላች።”—ዘኁልቁ 16:19-22, 35c
-
-
ለመለኮታዊ ሥልጣን በታማኝነት ተገዙመጠበቂያ ግንብ—2002 | ነሐሴ 1
-
-
c በፓትርያርኮች ዘመን እያንዳንዱ የቤተሰብ ራስ ሚስቱንና ልጆቹን ወክሎ በአምላክ ፊት ከመቅረቡም በላይ እነሱን ወክሎ መሥዋዕት ያቀርብ ነበር። (ዘፍጥረት 8:20፤ 46:1፤ ኢዮብ 1:5) ይሁን እንጂ ሕጉ ከተሰጠ በኋላ ይሖዋ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉና መሥዋዕት እንዲያቀርቡ የአሮንን ቤተሰብ ወንዶች ልጆች ሾመ። እነዚህ 250 የሚሆኑ ዓመፀኞች ከዚህ የአሠራር ለውጥ ጋር ለመተባበር ፈቃደኞች አለመሆናቸውን በግልጽ አሳይተዋል።
-