-
ዮፍታሔ ለይሖዋ የተሳለውን ፈጽሟልመጠበቂያ ግንብ—2007 | ግንቦት 15
-
-
በእስራኤል የነበረ አስቸጋሪ ሁኔታ
ዮፍታሔ የኖረው በአስቸጋሪ ዘመን ነው። ወገኖቹ የሆኑት እስራኤላውያን ንጹሑን አምልኮ ትተው የሲዶናን፣ የሞዓብን፣ የአሞንንና የፍልስጥኤማውያንን አማልክት ያመልኩ ነበር። በመሆኑም ይሖዋ ሕዝቡን ለ18 ዓመት በጭቆና ለገዟቸው ለአሞናውያንና ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ሰጣቸው። በዚህ ወቅት በተለይም ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ የሚኖሩት የገለዓድ ምድር ነዋሪዎች ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል።a በመጨረሻም እስራኤላውያን ወደ ልቦናቸው ተመልሰው ንስሐ በመግባት የይሖዋን እርዳታ ጠየቁ። እንዲሁም ባዕድ አማልክትን ከመካከላቸው በማስወገድ ይሖዋን ማምለክ ጀመሩ።—መሳፍንት 10:6-16

a አሞናውያን አረመኔያዊ ድርጊት ከመፈጸም ወደኋላ የሚሉ አልነበሩም። ከ60 ዓመት ገደማ በኋላ እንኳ በገለዓድ ከተሞች የሚኖሩትን ሰዎች ቀኝ ዓይን እንደሚያወጡ ዝተው እንደነበር ተዘግቧል። ነቢዩ አሞጽ አሞናውያን የገለዓድን ነፍሰ ጡር ሴቶች ሆድ የቀደዱበት ጊዜ እንደነበር ተናግሯል።—1 ሳሙኤል 11:2፤ አሞጽ 1:13
-