-
“ምግባረ መልካም ሴት”በእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
22, 23. (ሀ) ቦዔዝ ለሩት የሰጣት ስጦታ ምን ትርጉም ሊኖረው ይችላል? (የግርጌ ማስታወሻውንም ተመልከት።) (ለ) ኑኃሚን ሩትን ምን እንድታደርግ ነገረቻት?
22 ሩት ቤት ስትደርስ ኑኃሚን “ልጄ፣ አንቺ ማነሽ?” አለቻት። ምናልባትም ኑኃሚን እንዲህ ብላ የጠየቀቻት በደንብ ስላልነጋ ማንነቷን መለየት አቅቷት ሊሆን ይችላል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ኑኃሚን፣ ሩት እንደ ቀድሞዋ ብቸኛ መበለት ናት ወይስ የሚያገባት ሰው አግኝታለች የሚለውን ማወቅ ፈልጋ ይሆናል። ከዚያም ሩት ከቦዔዝ ጋር የተነጋገሩትን በሙሉ ለአማቷ ነገረቻት። በተጨማሪም ቦዔዝ ለኑኃሚን የላከላትን ገብስ ሰጠቻት።c—ሩት 3:16, 17 NW
-
-
“ምግባረ መልካም ሴት”በእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
c ቦዔዝ ለሩት ስድስት መስፈሪያ (መለኪያው አልተገለጸም) ገብስ መስጠቱ፣ ከስድስት የሥራ ቀናት በኋላ የሰንበት እረፍት እንደሚኖር ሁሉ ሩትም በመበለትነት ያሳለፈችው የልፋት ዘመን አብቅቶ ባል ማግባትና ኑሮ መመሥረት የሚያስገኘውን እረፍት የምታጣጥምበት ጊዜ እንደቀረበ ለመጠቆም ብሎ ሊሆን ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ ምናልባትም በላይዳ እየዛቀ የሰጣት ገብስ ስድስት መስፈሪያ ብቻ የሆነው ሩት ከዚያ በላይ ልትሸከም ስለማትችል ሊሆን ይችላል።
-