-
“ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ”በእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
16-18. (ሀ) ሩት ጽኑ ፍቅር እንደነበራት ያሳየችው እንዴት ነው? (ለ) ጽኑ ፍቅር ማሳየትን በተመለከተ ከሩት ምን ልንማር እንችላለን? (በተጨማሪም የሁለቱን ሴቶች ሥዕል ተመልከት።)
16 ሩት በዚያ ጭር ያለ መንገድ ላይ ኑኃሚንን ስትመለከታት ትታት ላለመሄድ በልቧ ወስና ነበር። ሩት ለኑኃሚንም ሆነ ኑኃሚን ለምታመልከው አምላክ በውስጧ ከፍተኛ ፍቅር ተተክሏል። ስለዚህ እንዲህ አለቻት፦ “ተለይቼሽ እንድቀር ወይም እንድመለስ አትለማመጭኝ፤ ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ፤ በምትኖሪበትም እኖራለሁ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፤ አምላክሽ አምላኬ ይሆናል። በምትሞቺበት እሞታለሁ፤ እዚያው እቀበራለሁ። ከእንግዲህ ሞት ከሚለየን በቀር ብለይሽ እግዚአብሔር [“ይሖዋ፣” NW] ይፍረድብኝ፤ ከዚህም የከፋ ያድርግብኝ።”—ሩት 1:16, 17
“ሕዝብሽ ሕዝቤ፤ አምላክሽ አምላኬ ይሆናል”
17 ሩት ከሞተች 3,000 የሚያህሉ ዓመታት ቢያልፉም የተናገረቻቸው ቃላት በጣም አስደናቂ ከመሆናቸው የተነሳ ዛሬም ድረስ ይታወሳሉ። እነዚህ ቃላት አንድን ግሩም ባሕርይ ይኸውም ጽኑ ፍቅርን ጥሩ አድርገው ይገልጻሉ። ሩት እጅግ ጥልቅና ጽኑ ፍቅር ስለነበራት ኑኃሚን በሄደችበት ሁሉ ከእሷ ላለመለየት ቆርጣ ነበር። ከሞት በቀር ምንም ነገር ሊለያቸው አይችልም። ሩት የሞዓባውያንን አማልክት ጨምሮ በሞዓብ የነበራትን ሁሉ ትታ ለመሄድ ዝግጁ ስለነበረች የኑኃሚን ሕዝቦች የእሷም ሕዝቦች ይሆናሉ። በመሆኑም ከዖርፋ በተለየ መልኩ ሩት የኑኃሚን አምላክ የሆነው ይሖዋ ለእሷም አምላኳ እንዲሆንላት እንደምትፈልግ በሙሉ ልብ መናገር ትችላለች።a
-
-
“ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ”በእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
a እስራኤላውያን ያልሆኑ አብዛኞቹ ሰዎች እንደሚያደርጉት ሩት “አምላክ” የሚለውን የማዕረግ ስም ብቻ አለመጠቀሟ ትኩረት የሚስብ ነው፤ ይሖዋ የሚለውን የአምላክን የግል ስም ተጠቅማለች። ዚ ኢንተርፕሪተርስ ባይብል እንደሚከተለው የሚል አስተያየት ሰጥቷል፦ “ጸሐፊው በዚህ መንገድ ይህች የባዕድ አገር ሴት እውነተኛውን አምላክ የምታመልክ መሆኗን ጎላ አድርጎ ገልጿል።”
-