የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ”
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ሐምሌ 1
    • ኮሽታ እንኳ በማይሰማበት በዚያ ጭር ያለ መንገድ ላይ ሳሉ ሩት ምን እንደምትፈልግ አሳምራ ታውቅ ነበር። ልቧ ለኑኃሚን እንዲሁም ኑኃሚን ለምታመልከው አምላክ ባላት ፍቅር ተሞልቶ ነበር። ስለዚህ እንዲህ አለቻት፦ “ተለይቼሽ እንድቀር ወይም እንድመለስ አትለማመጭኝ፤ ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ፤ በምትኖሪበትም እኖራለሁ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፤ አምላክሽ አምላኬ ይሆናል። በምትሞቺበት እሞታለሁ፤ እዚያው እቀበራለሁ። ከእንግዲህ ሞት ከሚለየን በቀር ብለይሽ እግዚአብሔር ይፍረድብኝ፤ ከዚህም የከፋ ያድርግብኝ።”​—ሩት 1:16, 17

      ሩት የተናገረቻቸው ቃላት በጣም አስደናቂ ናቸው፤ በመሆኑም እሷ ከሞተች 3,000 የሚያህሉ ዓመታት ቢያልፉም የተናገረችው ነገር ዛሬም ድረስ ይታወሳል። እነዚህ ቃላት ሩት ያላትን ግሩም ባሕርይ ይኸውም ጽኑ ፍቅሯን ጥሩ አድርገው ይገልጻሉ። ሩት የነበራት ፍቅር እጅግ ጠንካራና ጽኑ በመሆኑ ኑኃሚን በሄደችበት ሁሉ ከእሷ ላለመለየት ቆርጣለች። ሁለቱን ሊነጣጥላቸው የሚችለው ሞት ብቻ ነው። ሩት የሞዓባውያንን አማልክት ጨምሮ በሞዓብ የነበራትን ሁሉ ትታ ለመሄድ ዝግጁ ስለነበረች የኑኃሚን ሕዝቦች የእሷም ሕዝቦች ይሆናሉ። ከዖርፋ በተለየ መልኩ ሩት የኑኃሚን አምላክ የሆነው ይሖዋ ለእሷም አምላኳ እንዲሆንላት እንደምትፈልግ በሙሉ ልብ መናገር ትችላለች።b

  • “ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ”
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ሐምሌ 1
    • b እስራኤላዊ ያልሆኑ ብዙ ሰዎች እንደሚያደርጉት ሩት “አምላክ” የሚለውን የማዕረግ ስም ብቻ አለመጠቀሟ ትኩረት የሚስብ ነው፤ በበኩረ ጽሑፉ ላይ ይሖዋ የሚለውን የአምላክን የግል ስምም ተጠቅማለች። ዚ ኢንተርፕሪተርስ ባይብል እንደሚከተለው የሚል ሐሳብ ይዟል፦ “የሩት መጽሐፍ ጸሐፊ ይህች የባዕድ አገር ሴት የእውነተኛው አምላክ አምላኪ መሆኗን በዚህ መንገድ ጎላ አድርጎ ገልጿል።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ