የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ምግባረ መልካም ሴት”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • 7, 8. (ሀ) ኑኃሚን ቦዔዝ ደግነት እንዲያሳይ ያነሳሳው ማን እንደሆነ ተሰምቷት ነበር? ለምንስ? (ለ) ሩት ለአማቷ ያላት ጽኑ ፍቅር እንዳልቀነሰ ያሳየችው እንዴት ነው?

      7 ከዚያም በጨዋታቸው መሃል ሩት ስለ ቦዔዝ ደግነት ለኑኃሚን ነገረቻት። ኑኃሚንም በዚህ ተደስታ “በጎነቱን ለሕያዋንም ሆነ ለሙታን ማድረጉን ያልተወ እግዚአብሔር ይባርከው” አለች። (ሩት 2:20) ኑኃሚን፣ ቦዔዝን ደግነት እንዲያሳይ ያነሳሳው አገልጋዮቹ ለጋሶች እንዲሆኑ የሚያበረታታውና ሕዝቦቹ ለሚያሳዩት ደግነት ወሮታ እንደሚከፍል ቃል የገባው ይሖዋ እንደሆነ ገብቷታል።a—ምሳሌ 19:17⁠ን አንብብ።

  • “ምግባረ መልካም ሴት”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • a ኑኃሚን እንደገለጸችው ይሖዋ ደግነት የሚያሳየው በሕይወት ላሉት ብቻ ሳይሆን ለሞቱትም ጭምር ነው። ኑኃሚን ባሏንና ሁለቱን ወንዶች ልጆቿን በሞት አጥታለች። ሩትም ባሏን በሞት ተነጥቃለች። እነዚያ ሦስት ወንዶች በሁለቱ ሴቶች ሕይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ እንደነበራቸው ጥርጥር የለውም። ለሩትና ለኑኃሚን የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ደግነት እነዚህ ሴቶች ጥሩ እንክብካቤ እንዲደረግላቸው ይፈልጉ ለነበሩት ለእነዚያ ወንዶች እንደተደረገ የሚቆጠር ነው።

      b ከውርስ ጋር በተያያዘ እንደሚደረገው ሁሉ በዚህ ጊዜም ባሏ የሞተባትን ሴት የማግባት መብት በመጀመሪያ ለሟቹ ወንድሞች ይሰጣል፤ እነሱ ይህን ማድረግ ካልቻሉ ደግሞ ይህ መብት የቅርብ ዘመዱ ለሆነ ወንድ ይሰጥ ነበር።—ዘኍ. 27:5-11

  • “ምግባረ መልካም ሴት”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • 11, 12. (ሀ) ኑኃሚን፣ ቦዔዝ “የመቤዠት ግዴታ” እንዳለበት ስትገልጽ በአምላክ ሕግ ውስጥ የተካተተውን የትኛውን ፍቅራዊ ዝግጅት መጥቀሷ ነው? (ለ) ሩት አማቷ ለለገሰቻት ምክር ምን ምላሽ ሰጠች?

      11 ሩት ስለ ቦዔዝ ለኑኃሚን መጀመሪያ ስትነግራት ኑኃሚን “ሰውየው እኮ የሥጋ ዘመዳችን ነው፤ የመቤዠት ግዴታ ካለባቸው ዘመዶቻችን አንዱ እርሱ ነው” ብላት ነበር። (ሩት 2:20) ኑኃሚን ምን ማለቷ ነበር? አምላክ ለእስራኤላውያን የሰጠው ሕግ፣ በድህነትም ሆነ የቤተሰብ አባልን በሞት በማጣት የተነሳ ችግር ላይ የወደቁ ቤተሰቦችን የሚጠቅም ፍቅራዊ ዝግጅት ይዟል። አንዲት ሴት፣ ልጅ ሳትወልድ ባሏ ቢሞት ሐዘኗ የከፋ ይሆናል፤ ምክንያቱም ባሏ ዘር ሳይተካ ስለሞተ ወደፊት በስሙ የሚጠራ ዘር አይኖረውም። ይሁን እንጂ አምላክ ያወጣው ሕግ ይህች ሴት የባሏን ወንድም አግብታ የሟቹን ስም የሚያስጠራና የቤተሰቡን ንብረት የሚወርስ ልጅ እንድትወልድ ይፈቅድ ነበር።b—ዘዳ. 25:5-7

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ