የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ምግባረ መልካም ሴት”
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥቅምት 1
    • ብዙም ሳይቆይ ሁለቱ ሴቶች የጦፈ ጨዋታ ያዙ፤ በዚህ መሃል ሩት ስለ ቦዔዝ ደግነት ለኑኃሚን ነገረቻት። ኑኃሚን በዚህ ተደስታ “በጎነቱን ለሕያዋንም ሆነ ለሙታን ማድረጉን ያልተወ እግዚአብሔር ይባርከው” አለች። (ሩት 2:19, 20) ኑኃሚን፣ ቦዔዝ ደግነት እንዲያሳይ ያነሳሳው ይሖዋ እንደሆነ ተገንዝባ ነበር፤ ይሖዋ አገልጋዮቹ ለጋሶች እንዲሆኑ የሚገፋፋቸው ከመሆኑም ሌላ ሕዝቦቹ ለሚያሳዩት ደግነት ወሮታቸውን እንደሚከፍል ቃል ገብቷል።b—ምሳሌ 19:17

  • “ምግባረ መልካም ሴት”
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥቅምት 1
    • ሩት ስለ ቦዔዝ ለኑኃሚን መጀመሪያ ስትነግራት ኑኃሚን “ሰውየው እኮ የሥጋ ዘመዳችን ነው፤ የመቤዠት ግዴታ ካለባቸው ዘመዶቻችን አንዱ እርሱ ነው” ብላት ነበር። (ሩት 2:20) ኑኃሚን ምን ማለቷ ነበር? አምላክ ለእስራኤል የሰጠው ሕግ፣ በድህነትም ሆነ የቤተሰብ አባልን በሞት በማጣት የተነሳ ችግር ላይ የወደቁ ቤተሰቦችን የሚጠቅም ፍቅራዊ ዝግጅት ይዟል። አንዲት ሴት፣ ልጅ ሳትወልድ ባሏ ቢሞት ሐዘኗ የከፋ ይሆናል፤ ምክንያቱም ባሏ ዘር ሳይተካ ስለሞተ ወደፊት በስሙ የሚጠሩ ዘሮች አይኖሩትም። ይሁን እንጂ ይህች ሴት የባሏን ወንድም አግብታ የሟቹን ስም የሚያስጠራና የቤተሰቡን ንብረት የሚወርስ ልጅ ለመውለድ የሚያስችላት ዝግጅት በአምላክ ሕግ ውስጥ ተካትቶ ነበር።c—ዘዳግም 25:5-7

  • “ምግባረ መልካም ሴት”
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥቅምት 1
    • b ኑኃሚን እንደገለጸችው ይሖዋ ደግነት የሚያሳየው በሕይወት ላሉት ብቻ ሳይሆን ለሞቱትም ጭምር ነው። ኑኃሚን ባሏንና ሁለቱንም ወንዶች ልጆቿን በሞት አጥታለች። ሩትም ባሏን በሞት ተነጥቃለች። እነዚያ ሟች ሦስት ወንዶች በሁለቱ ሴቶች ሕይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ እንደነበራቸው ጥርጥር የለውም። ሟቾቹ፣ ኑኃሚንን እና ሩትን ይወዷቸው ስለነበር እንክብካቤ እንዲደረግላቸው እንደሚፈልጉ የታወቀ ነው፤ በመሆኑም ለእነዚህ ሴቶች የሚደረግ ማናቸውም የደግነት ድርጊት ለሟቾቹ እንደተደረገ የሚቆጠር ነው።

      c ከውርስ ጋር በተያያዘ እንደሚደረገው ሁሉ በዚህ ጊዜም ባሏ የሞተባትን ሴት የማግባት መብት በመጀመሪያ ለሟቹ ወንድሞች ይሰጣል፤ እነሱ ይህን ማድረግ ካልቻሉ ደግሞ ይህ መብት የቅርብ ዘመዱ ለሆነ ወንድ ይተላለፍ ነበር።—ዘኍልቍ 27:5-11

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ