የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ለይሖዋ እንደ ልቡ የሆነለት ሰው
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | መስከረም 1
    • የዳዊት ሥራ ለአደጋ የሚያጋልጥ ነበር። ከእነዚህ ኮረብቶች በአንዱ ላይ ከመንጋው መካከል በግ ነጥቆ ሊሄድ የሞከረ አንበሳና ድብ አጋጥሞት ያውቃል።a ይህ ደፋር ልጅ አውሬዎቹን አሳድዶ በመግደል በጎቹን ከአፋቸው አስጥሏል። (1 ሳሙኤል 17:34-36) ምናልባትም ዳዊት ወንጭፍ የመጠቀም ችሎታውን ያዳበረው በዚህ ወቅት ሊሆን ይችላል። ከመኖሪያ ከተማው ብዙም ሳይርቅ የብንያም ክልል ይገኛል። የብንያም ሰዎች ደግሞ “ድንጋይ ወንጭፈው ጠጕር እንኳ የማይስቱ” ተዋጊዎች ነበሩ። ዳዊትም ቢሆን ወንጭፍ ሲጠቀም እንደ እነሱ ዒላማውን አይስትም ነበር።​—መሳፍንት 20:14-16፤ 1 ሳሙኤል 17:49

  • ለይሖዋ እንደ ልቡ የሆነለት ሰው
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | መስከረም 1
    • a ቀድሞ በፓለስቲና ይገኝ የነበረው ቡናማ ቀለም ያለው የሶርያ ድብ፣ በአማካይ 140 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሲሆን ትልቅ በሆነው መዳፉ በመምታት ብቻ አንድን ሰው ወይም እንስሳ መግደል ይችላል። በወቅቱ በዚህ አካባቢ በርካታ አንበሶች ይኖሩ ነበር። ኢሳይያስ 31:4 “ብዙ እረኞች” እንኳ አንድ “የአንበሳ ደቦል” የያዘውን እንስሳ ማስጣል እንደማይችሉ ይናገራል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ