-
‘የተሰበረና የተዋረደ ልብ’ ያላቸው ሰዎች ምሕረት በሚፈልጉበት ጊዜመጠበቂያ ግንብ—2010 | ግንቦት 1
-
-
ዳዊት ራሱን ነፃ ለማድረግ ሰበብ እንዳይፈጥር ሲል ከዚህ ቀደም እረኛ የነበረውን የዳዊትን ልብ እንደሚነካ እርግጠኛ የሆነበትን አንድ ታሪክ ነገረው። ታሪኩ ስለ አንድ ባለጠጋና ስለ አንድ ድሃ የሚናገር ነበር። ባለጠጋው “እጅግ ብዙ በጎችና የቀንድ ከብቶች” የነበሩት ሲሆን ድሃው ግን “አንዲት ጠቦት” ብቻ ነበረችው። ባለጠጋው እንግዳ ስለመጣበት ምግብ ማዘጋጀት ፈለገ። ከራሱ በጎች መካከል ወስዶ ከማዘጋጀት ይልቅ ድሃው ያለችውን አንዲት ጠቦት ወሰደ። ዳዊት የተነገረው ታሪክ እውነት መስሎት መሆን አለበት በጣም ተቆጥቶ “ይህን ያደረገው ሰው ሞት ይገባዋል!” በማለት ተናገረ። ለምን? ዳዊት ምክንያቱን ሲናገር ‘ሐዘኔታ’ አላሳየም በማለት ገልጿል።a—ቁጥር ከ2-6
-