የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የሥጋ መውጊያቸውን ተቋቁመው ኖረዋል
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | የካቲት 15
    • 11. ሲባ ሜምፊቦስቴን በማስመልከት ምን ተናገረ? ሆኖም የተናገረው ውሸት መሆኑን እንዴት እናውቃለን? (የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት።)

      11 ከጊዜ በኋላ ሜምፊቦስቴ ከሌላ የሥጋ መውጊያ ጋር መታገል አስፈልጎት ነበር። ንጉሥ ዳዊት ልጁ አቤሴሎም በእርሱ ላይ በማመፁ ምክንያት ከኢየሩሳሌም ሸሽቶ ሳለ አገልጋዩ ሲባ በንጉሡ ፊት የሜምፊቦስቴን ስም አጠፋ። ሜምፊቦስቴ ታማኝነቱን እንዳጎደለና ንግሥና አገኛለሁ በሚል በኢየሩሳሌም እንደቀረ ሲባ ተናገረ።a ዳዊት የሲባን የሐሰት ወሬ በማመን የሜምፊቦስቴን ንብረት በሙሉ በመውሰድ ለዚህ ውሸታም ሰው ሰጠው።​—⁠2 ሳሙኤል 16:1-4

  • የሥጋ መውጊያቸውን ተቋቁመው ኖረዋል
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | የካቲት 15
    • a ሜምፊቦስቴ አድናቂና ትሑት ሰው ስለነበር ሥልጣን ለማግኘት ሲል እንዲህ ያለ እርምጃ ይወስዳል ብሎ ማመን ያስቸግራል። የአባቱን የዮናታንን የታማኝነት ታሪክ እንደሚያውቅ ምንም ጥርጥር የለውም። ዮናታን የንጉሥ ሳኦል ልጅ የነበረ ቢሆንም እንኳ ይሖዋ በእስራኤል ላይ እንዲነግሥ የመረጠው ዳዊትን እንደሆነ በትህትና አምኖ ተቀብሏል። (1 ሳሙኤል 20:12-17) ዮናታን ፈሪሃ አምላክ የነበረው የሜምፊቦስቴ ወላጅና የዳዊት ታማኝ ወዳጅ እንደመሆኑ መጠን ልጁ ንጉሣዊ ሥልጣን እንዲመኝ አያስተምረውም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ