-
በንቃትና በትዕግሥት ተጠባብቋልበእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
17, 18. (ሀ) ኤልያስ ወደ ኢይዝራኤል ሲሄድ በመንገድ ላይ ምን አጋጠመው? (ለ) ኤልያስ ከቀርሜሎስ ወደ ኢይዝራኤል እየሮጠ መሄዱ አስደናቂ ነው የምንለው ለምንድን ነው? (የግርጌ ማስታወሻውንም ተመልከት።)
17 የይሖዋ ነቢይ፣ አክዓብ የሄደበትን መንገድ ተከትሎ መጓዝ ጀመረ። ረጅም፣ በጨለማ የተዋጠና የጨቀየ መንገድ ከፊቱ ይጠብቀዋል። ሆኖም አንድ ያልተጠበቀ ነገር ተከሰተ።
18 “የእግዚአብሔርም ኀይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን ከፍ አድርጎ በቀበቶው ካጠበቀ በኋላ እስከ ኢይዝራኤል ድረስ በአክዓብ ፊት ሮጠ።” (1 ነገ. 18:46) ከዚህ በግልጽ መረዳት እንደሚቻለው የይሖዋ ኃይል በተለየ መንገድ በኤልያስ ላይ እየሠራ ነበር። ኢይዝራኤል የምትገኘው 30 ኪሎ ሜትር ገደማ ላይ ሲሆን ኤልያስ ደግሞ ዕድሜው ገፍቷል።a ይህ ነቢይ እንደ ልብ ለመሮጥ እንዲያመቸው የለበሰውን ረጅም መጎናጸፊያ ሰብሰብ አድርጎ ወገቡ ላይ በቀበቶው ሸብ በማድረግ በጨቀየው መንገድ ላይ ሲሮጥ በዓይነ ሕሊናህ ይታይህ። እሱም በከፍተኛ ፍጥነት በመሮጥ የቤተ መንግሥቱ ሠረገላ ላይ ደረሰበት፤ ከዚያም አልፎት ሄደ!
19. (ሀ) ኤልያስ ከአምላክ ያገኘው ኃይልና ጥንካሬ የትኞቹን ትንቢቶች ያስታውሰናል? (ለ) ኤልያስ ወደ ኢይዝራኤል እየሮጠ ሲሄድ ስለ ምን ነገር እርግጠኛ ነበር?
19 ይህ ለኤልያስ እንዴት ያለ በረከት ነበር! እንዲህ የመሰለ ምናልባትም በወጣትነት ጊዜው ተሰምቶት የማያውቀው ዓይነት ኃይል፣ ጥንካሬና ብርታት ሲሰማው ምን ያህል ተደስቶ ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ይህ ሁኔታ ታማኝ የይሖዋ አገልጋዮች ወደፊት ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ፍጹም የሆነ ጤንነትና ብርታት እንደሚያገኙ ዋስትና የሚሰጡትን ትንቢቶች አስታውሶን ይሆናል። (ኢሳይያስ 35:6ን አንብብ፤ ሉቃስ 23:43) ኤልያስ በዚያ በጨቀየ መንገድ ላይ ሲሮጥ፣ ብቻውን እውነተኛ አምላክ የሆነውን የአባቱን የይሖዋን ሞገስ እንዳገኘ ተገንዝቦ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም!
-
-
አምላኩ አጽናንቶታልበእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
1, 2. ኤልያስ ፈጽሞ ሊረሳው በማይችለው በዚያ ታሪካዊ ዕለት ምን ነገር ተከናወነ?
ኤልያስ፣ ሰማዩ ይበልጥ እየጨላለመ ቢመጣም በዝናቡ ውስጥ መሮጡን አላቆመም። ኢይዝራኤል ለመድረስ ገና ብዙ መንገድ ይቀረዋል፤ በዚያ ላይ ደግሞ ኤልያስ በዕድሜ የገፋ ሰው ነው። ያም ሆኖ የይሖዋ ኃይል በእሱ ላይ ስለወረደ ምንም ዓይነት የድካም ስሜት ሳይታይበት መሮጡን ተያይዞታል። ጭራሽ፣ አክዓብ የተቀመጠበትን የቤተ መንግሥት ሠረገላ የሚጎትቱትን ፈረሶች ቀድሟቸው ሄደ! ኤልያስ ከዚህ በፊት እንደዚህ ያለ ብርታት አግኝቶ እንደማያውቅ ጥርጥር የለውም።—1 ነገሥት 18:46ን አንብብ።
-