የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አምላኩ አጽናንቶታል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • 20, 21. (ሀ) ኤልያስ በኮሬብ ተራራ በሚገኘው ዋሻ ደጃፍ ላይ ሆኖ ምን እንደተመለከተ ግለጽ። (ለ) ኤልያስ የይሖዋን ኃይል የሚያሳዩ ትዕይንቶችን መመልከቱ ምን እንዲገነዘብ ረድቶታል?

      20 ይሖዋ የኤልያስን ፍርሃትና ጭንቀት ለማስወገድ ምን አደረገ? መልአኩ ኤልያስን በዋሻው መግቢያ ላይ እንዲቆም ነገረው። ኤልያስ ቀጥሎ ምን እንደሚከናወን ባያውቅም እንደታዘዘው አደረገ። በድንገት ኃይለኛ ነፋስ ነፈሰ! በዚህ ጊዜ ጆሮ የሚያደነቁር ድምፅ ተሰምቶ መሆን አለበት፤ ምክንያቱም ነፋሱ በጣም ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ ተራሮቹና ዐለቶቹ ተሰነጣጥቀዋል። ኤልያስ በአንድ እጁ ነፋሱ ፀጉራም ካባውን ከላዩ ላይ ገፍፎ እንዳይወስድበት ሙጭጭ አድርጎ ይዞ በሌላኛው እጁ ዓይኑን ለመከለል ሲሞክር በዓይነ ሕሊናህ ይታይህ። ከዚያም የመሬት መንቀጥቀጥ አካባቢውን አናወጠው፤ በዚህ ወቅት ኤልያስ ሚዛኑን ለመጠበቅ ምን ያህል ትግል እንደሚያደርግ ለማሰብ ሞክር! ከዚያም ኤልያስ ገና ሳይረጋጋ ኃይለኛ የእሳት ወላፈን አካባቢውን ገረፈው፤ በመሆኑም ኤልያስ ራሱን ከእሳቱ ወላፈን ለማዳን ዋሻው ውስጥ ዘሎ ገባ።—1 ነገ. 19:11, 12

      ኤልያስ በአንድ ዋሻ አፍ ላይ ቆሞ እሳቱ እንዳያገኘው ሲከለል

      ይሖዋ ኤልያስን ለማጽናናትና ለማበረታታት እጅግ ታላቅ የሆነውን ኃይሉን ተጠቅሟል

      21 ሦስቱም ሁኔታዎች በተከሰቱበት ወቅት ይሖዋ በእነዚያ አስደናቂ የተፈጥሮ ኃይሎች ውስጥ እንዳልነበር ዘገባው ይነግረናል። ኤልያስ፣ ይሖዋ አምላኪዎቹ “ደመና ጋላቢ” ወይም ዝናብ አምጪ እንደሆነ በማሰብ ክብር እንደሚሰጡት እንደ በኣል ያለ በተፈጥሮ ኃይሎች ውስጥ የሚገኝ ምናብ የወለደው አምላክ እንዳልሆነ ያውቅ ነበር። ይሖዋ በጣም አስደናቂ የሆኑት የተፈጥሮ ኃይሎች ሁሉ ምንጭ ከመሆኑም በላይ እሱ ከሠራው ከማንኛውም ነገር እጅግ የላቀ ነው። ግዑዝ የሆኑት ሰማያትም እንኳ ሊይዙት አይችሉም! (1 ነገ. 8:27) ታዲያ ኤልያስ ይህን ሁሉ መመልከቱ የጠቀመው እንዴት ነው? ኤልያስ ምን ያህል ፈርቶ እንደነበር አስታውስ። ታዲያ ኤልያስ፣ በፈለገው ጊዜ ሊጠቀምበት የሚችል ይህ ነው የማይባል ኃይል ያለው ይሖዋ ከጎኑ እያለለት አክዓብንም ሆነ ኤልዛቤልን የሚፈራበት ምን ምክንያት አለ?—መዝሙር 118:6⁠ን አንብብ።

      22. (ሀ) ‘ለስለስ ያለው ድምፅ’ ኤልያስ ዋጋ ቢስ አለመሆኑን እንዲገነዘብ የረዳው እንዴት ነው? (ለ) ‘ለስለስ ያለው ድምፅ’ ምንጭ ማን ሊሆን ይችላል? (የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት።)

      22 እሳቱ እንዳለፈ ጸጥታ ሰፈነ፤ ከዚያም ኤልያስ “ለስለስ ያለ ድምፅ” ሰማ። ድምፁም ኤልያስ ስሜቱን በድጋሚ እንዲገልጽ የሚያበረታታ ነበር፤ ስለሆነም ኤልያስ ያስጨነቀውን ነገር ለሁለተኛ ጊዜ ግልጥልጥ አድርጎ ተናገረ።a ምናልባትም እንዲህ ማድረጉ ይበልጥ ቀለል እንዲለው ሳያደርገው አልቀረም። ያም ሆኖ ‘ለስለስ ያለው ድምፅ’ ቀጥሎ የተናገረው ሐሳብ ኤልያስን ይበልጥ አጽናንቶት እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ይሖዋ፣ ኤልያስ እሱ እንዳሰበው ዋጋ ቢስ አለመሆኑን እንዲገነዘብ ረዳው። ይህን ያደረገው እንዴት ነው? አምላክ የበኣል አምልኮን ከእስራኤል ምድር ለማስወገድ ከሚደረገው ጦርነት ጋር በተያያዘ ወደፊት ምን ለማድረግ እንዳሰበ ገለጸለት። በግልጽ ማየት እንደሚቻለው የአምላክ ዓላማ አንዳች የሚገታው ነገር ሳይኖር ወደፊት በመገስገስ ላይ ስለሆነ የኤልያስ ልፋት ከንቱ ሆኖ አልቀረም። ከዚህም በላይ ይሖዋ ለኤልያስ አንዳንድ ዝርዝር መመሪያዎችን በመስጠት እንደገና ወደ ሥራው እንዲመለስ ስላደረገው ይህ ነቢይ አሁንም ቢሆን በይሖዋ ዓላማ ውስጥ የሚጫወተው ሚና አለ።—1 ነገ. 19:12-17

  • አምላኩ አጽናንቶታል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • a የዚህ “ለስለስ ያለ ድምፅ” ምንጭ በ⁠1 ነገሥት 19:9 ላይ የተጠቀሰውን የይሖዋን “ቃል” እንዲያደርስ የተላከው መንፈሳዊ አካል ራሱ ሳይሆን አይቀርም። በቁጥር 15 (NW) ላይ ይህ መንፈሳዊ አካል “ይሖዋ” ተብሎ ተጠርቷል። ይህም ይሖዋ እስራኤላውያንን በምድረ በዳ ለመምራት የተጠቀመበትንና “ስሜ በርሱ ላይ ነው” በማለት የተናገረለትን መንፈሳዊ አካል ያስታውሰን ይሆናል። (ዘፀ. 23:21) እውነት ነው፣ ስለዚህ ጉዳይ በእርግጠኝነት መናገር አንችልም፤ ያም ሆኖ ኢየሱስ ሰው ከመሆኑ በፊት “ቃል” ማለትም ለይሖዋ አገልጋዮች ልዩ ቃል አቀባይ ሆኖ እንዳገለገለ ልብ ማለት ይገባል።—ዮሐ. 1:1

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ