የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አምላኩ አጽናንቶታል
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | ሐምሌ 1
    • ይሖዋ የኤልያስን ፍርሃትና ጭንቀት ለማስወገድ ምን አደረገ? መልአኩ፣ ኤልያስ በዋሻው መግቢያ ላይ እንዲቆም ነገረው። ኤልያስ ቀጥሎ ምን እንደሚከናወን ባያውቅም እንደታዘዘው አደረገ። በድንገት ኃይለኛ ነፋስ ነፈሰ! በዚህ ጊዜ ጆሮ የሚያደነቁር ድምፅ ተሰምቶ መሆን አለበት፤ ምክንያቱም ነፋሱ በጣም ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ ተራሮቹና ዐለቶቹ ተሰነጣጥቀዋል። ኤልያስ ነፋሱ ፀጉራም ካባውን ከላዩ ላይ ገፍፎ እንዳይወስድበት ሙጭጭ አድርጎ እንደያዘ ዓይኑን ለመከለል ሲሞክር በሐሳብህ ይታይህ። ከዚያም የመሬት መንቀጥቀጥ አካባቢውን አናወጠው፤ በዚህ ወቅት ኤልያስ ሚዛኑን ለመጠበቅ ምን ያህል ትግል እንደሚያደርግ ለማሰብ ሞክር! ከዚያም በመቀጠል ኃይለኛ እሳት በመነሳቱ ኤልያስ ወደ ዋሻው ዘሎ ገባ፤ በዚህም የተነሳ በወላፈኑ ከመበላት ለጥቂት ዳነ።​—1 ነገሥት 19:11, 12

      ሦስቱም ሁኔታዎች በተከሰቱበት ወቅት ይሖዋ በእነዚያ አስደናቂ የተፈጥሮ ኃይል መግለጫዎች ውስጥ እንዳልነበረ ዘገባው ይነግረናል። አምላኪዎቹ “ደመና ጋላቢ” ወይም ዝናብ አምጪ እንደሆነ በማሰብ ክብር እንደሚሰጡ እንደ በኣል ይሖዋ በተፈጥሮ ኃይሎች ውስጥ የሚገኝ ምናብ የወለደው አምላክ እንዳልሆነ ኤልያስ ያውቅ ነበር። ይሖዋ በአጽናፈ ዓለም ውስጥ የሚገኙት እጅግ ታላቅ የሆኑት የተፈጥሮ ኃይሎች ሁሉ ምንጭ ከመሆኑም በላይ እሱ ከሠራው ከማንኛውም ነገር የላቀ ኃይል አለው። ሰማያትም እንኳን እሱን ሊይዙት አይችሉም! (1 ነገሥት 8:27) ታዲያ ኤልያስ ይህን ሁሉ መመልከቱ የጠቀመው እንዴት ነው? ኤልያስ ምን ያህል ፈርቶ እንደነበር አስታውስ። ይሖዋ በፈለገው ጊዜ ሊጠቀምበት የሚችል ይህ ነው የማይባል ኃይል እንዳለው ኤልያስ ተመልክቷል፤ ታዲያ ይህን የመሰለ አምላክ ከጎኑ እያለለት አክዓብንም ሆነ ኤልዛቤልን የሚፈራበት ምንም ምክንያት አለ?​—መዝሙር 118:6

      እሳቱ እንዳለፈ ጸጥታ ሰፈነ፤ ከዚያም ኤልያስ “ለስለስ ያለ ድምፅ” ሰማ።b “ኤልያስ ሆይ፤ እዚህ ምን ታደርጋለህ?” የሚለው ለስለስ ባለ ድምፅ ለሁለተኛ ጊዜ የቀረበለት ጥያቄ ኤልያስ ስሜቱን በድጋሚ እንዲገልጽ የሚጋብዝ ነበር፤ እሱም ያስጨነቀውን ነገር ለሁለተኛ ጊዜ ግልጥልጥ አድርጎ ተናገረ። እንዲህ ማድረጉ ይበልጥ ቀለል እንዲለው ሳያደርገው አልቀረም። ኤልያስ ቀጥሎ የሰማው ‘ለስለስ ባለ ድምፅ’ የተነገረው ሐሳብ ግን ይበልጥ አጽናንቶት እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ይሖዋ፣ ኤልያስ እሱ እንዳሰበው ዋጋ ቢስ አለመሆኑን እንዲገነዘብ ረዳው። ይሖዋ ይህን ያደረገው እንዴት? አምላክ የበኣል አምልኮን ከእስራኤል ምድር ለማስወገድ ከሚደረገው ጦርነት ጋር በተያያዘ ወደፊት ምን ለማድረግ እንዳሰበ ገለጸለት። በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው የአምላክ ዓላማ አንዳች የሚገታው ነገር ሳይኖር ወደፊት በመገስገስ ላይ ስለሆነ የኤልያስ ልፋት ከንቱ ሆኖ አልቀረም። ከዚህም በላይ ይሖዋ ለኤልያስ አንዳንድ ዝርዝር መመሪያዎችን በመስጠት እንደገና ወደ ሥራው እንዲመለስ ስላደረገው ይህ ነቢይ አሁንም ቢሆን በይሖዋ ዓላማ ውስጥ ድርሻ ነበረው።​—1 ነገሥት 19:12-17

  • አምላኩ አጽናንቶታል
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | ሐምሌ 1
    • b የዚህ “ለስለስ ያለ ድምፅ” ምንጭ ይሖዋ በ⁠1 ነገሥት 19:9 ላይ የሚገኘውን ‘ቃሉን’ ለማስተላለፍ የተጠቀመበት መንፈሳዊ አካል ሳይሆን አይቀርም። ይህ መንፈሳዊ አካል የአምላክ ወኪል በመሆኑ በቁጥር 15 ላይ የተጠቀሰው “እግዚአብሔር” ተብሎ ነው። ይህም ይሖዋ እስራኤላውያንን በምድረ በዳ ለመምራት የተጠቀመበትንና “ስሜ በርሱ ላይ ነው” በማለት አምላክ የተናገረለትን መንፈሳዊ አካል ያስታውሰን ይሆናል። (ዘፀአት 23:21) እውነት ነው፣ ስለዚህ ጉዳይ በእርግጠኝነት መናገር አንችልም፤ ያም ሆኖ ኢየሱስ ሰው ከመሆኑ በፊት “ቃል” ማለትም ይሖዋ ከአገልጋዮቹ ጋር ባለው ግንኙነት ልዩ ቃል አቀባይ ሆኖ እንዳገለገለ ልብ ማለት ይገባል።​—ዮሐንስ 1:1

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ