-
‘ለመልካም ሥራ የምትቀኑ’ ሁኑ!መጠበቂያ ግንብ—2009 | ሰኔ 15
-
-
4, 5. አራቱ የይሁዳ ነገሥታት ለመልካም ሥራ ቀናተኛ መሆናቸውን ያሳዩት እንዴት ነው?
4 አሳ፣ ኢዮሣፍጥ፣ ሕዝቅያስና ኢዮስያስ ጣዖት አምልኮን ከይሁዳ ጠራርጎ ለማጥፋት ዘመቻ አካሂደዋል። አሳ “ባዕዳን መሠዊያዎችንና ማምለኪያ ኰረብታዎችን አስወገደ፤ ማምለኪያ ዐምዶችን አፈረሰ፤ አሼራ ለተባለች ጣዖት አምላክ የቆሙ የዕንጨት ቅርጽ ምስሎችንም ቈራረጠ።” (2 ዜና 14:3) ኢዮሣፍጥ ለይሖዋ አምልኮ የነበረው ከፍተኛ ቅንዓት “ማምለኪያ ኰረብታዎችንና የአሼራ ዐምዶችን ከይሁዳ [እንዲያስወግድ]” አነሳስቶታል።—2 ዜና 17:6፤ 19:3a
-
-
‘ለመልካም ሥራ የምትቀኑ’ ሁኑ!መጠበቂያ ግንብ—2009 | ሰኔ 15
-
-
a አሳ የሐሰት አምልኮ ይካሄድባቸው የነበሩ የማምለኪያ ኰረብታዎችን ሲያስወግድ ሕዝቡ ይሖዋን ያመልክባቸው የነበሩትን ኰረብታዎች አላጠፋ ይሆናል። ወይም ደግሞ የማምለኪያ ኰረብታዎቹ በእሱ የግዛት ዘመን መጨረሻ አካባቢ በድጋሚ የተገነቡና በኋላ ላይ ልጁ ኢዮሣፍጥ ያጠፋቸው ሊሆኑ ይችላሉ።—1 ነገ. 15:14፤ 2 ዜና 15:17
-