መጽሐፍ ቅዱስን ልትተማመንበት ትችላለህን?
መጽሐፍ ቅዱስን ብትገልጥና ብትመለከት ስለ ሳንቲም የሚናገር ቦታ የምታገኝ ይመስልሃልን? ከብር ስለተሠራው ስለዚህ ጥንታዊ ሳንቲም ምን ሊባል ይቻላል?
ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ደስ የሚሉ ታሪኮችና የሚደነቁ የግብረ ገብ ትምህርቶችን የሚሰጥ የጥንት መጽሐፍ እንደሆነ አድርገው ያስ ባሉ። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ በውስጡ የያዛቸውን ታሪኮች ትክክለኛነት ስለማያምኑ የአምላክ ቃል መሆኑን ይክዳሉ። ይሁን እንጂ የመጽሐፍ ቅዱስን ትክክለኛነት የሚያረጋግጥ በቂ ማስረጃ አለ። ይህ (ተለቅ ብሎ እንዲታይ የተደረገ) ሳንቲም ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው። እላዩ ላይ የተጻፈው ምን ይላል?
ሳንቲሙ የተሠራው ዛሬ ቱርክ ተብላ ከምትጠራው አገር ደቡባዊ ምሥራቅ በምትገኝ ጠርሴስ በምትባል ከ ተማ ነው። ሳንቲሙ የተቀረጸው በአራተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ የፋርስ ገዥ በነበረው በማዛዩስ ዘመነ መንግሥት ነበ ር። እሱንም “በወንዙ ማዶ” ማለትም ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ያለው ክፍለ ሀገር ገዥ በማለት ይጠቅሰዋል።
ይህን ሐረግ መጥቀስ ለምን አስፈለገ? ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስህ ውስጥ ተመሳሳይ አጠራር ስለምታገኝ ነው። ዕዝራ 5:6 እስከ 6:13 በፋርሱ ንጉሥ በዳርዮስ እና ተንትናይ በተባለው ገዥ መካከል ስለተደረገ መጻጻፍ ይጠቅሳል። ተነሥቶ የነበረው አጨቃጫቂ ጉዳይ አይሁዶች በኢየሩሳሌም ውስጥ ቤተ መቅደሳቸውን እንደገ ና መሥራታቸው ነበር። ዕዝራ የአምላክ ሕግ ፈጣን ጸሐፊ (ገልባጭ) ስለነበረ በሚጽፋቸው ነገሮች ሁሉ ጠንቃቃና ትክክለኛ እንደሚሆን አያጠራጥርም። በዕዝራ 5:6 እና 6:13 ላይ ተንትናይን “በወንዙ ማዶ የነበረው ገዥ” ብሎ እንደጠራው ትመለከታለህ።
ዕዝራ ይህን የጻፈው ሳንቲሙ ከመቀረጹ ከ100 ዓመት በፊት ማለትም በ460 ከዘአበ ነበር። አንዳንድ ሰዎች የአንድ ጥንታዊ ባለ ሥልጣን መጠቀስ ያን ያህል ትልቅ ነገር አይደለም ብለው በማሰብ አቃልለው ይናገሩ ይሆናል። የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎችን እንደዚህ በመሳሰሉ ጥቃቅን ነገሮች እንኳ ሳይቀር ልትተማመንባቸው ከቻልክ እነሱ በጻፏቸ ው ሌሎች የመጽሐፉ ክ ፍሎች ላይ ያለህ ትምክህ ት ሊጨምር አይገባውምን?
በዚህ እትም የመጀመሪያዎቹ ሁ ለት ርዕሰ ትምህርቶች ላይ ለዚህ ዓይነቱ ትምክ ህት መሠረት የሚሆኑ ተጨማሪ ምክንያቶችን ታገኛለህ።
[ምንጭ]
Collection of Israel Dept. of Antiquities Exhibited & photographed Israel Museum