-
ለአምላክ ሕዝብ ጥብቅና ቆማለችበእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
19. ሐማ ምን ለማድረግ ፈለገ? ንጉሡንስ ያግባባው እንዴት ነበር?
19 ይህ ሁኔታ ሐማን እጅግ አስቆጣው። ይሁንና መርዶክዮስን ማስገደል የሚችልበትን መንገድ መፈለግ ብቻ በቂ መስሎ አልታየውም። የመርዶክዮስን ወገኖች በሙሉ ለመደምሰስ ቆርጦ ተነሳ! በመሆኑም ሐማ ስለ አይሁዳውያን መጥፎ ወሬ በመናገር ንጉሡን አግባባው። ማንነታቸውን እንኳ ሳይጠቅስ በሕዝቡ መካከል ‘ተሠራጭተውና ተበታትነው የሚኖሩ’ ተራ ሰዎች እንደሆኑ አድርጎ ለንጉሡ ነገረው። ይባስ ብሎም ንጉሡ ያወጣቸውን ሕጎች እንደማያከብሩ ተናገረ፤ ይህ ከሆነ ደግሞ እነዚህ ሰዎች ስጋት የሚፈጥሩ ዓመፀኞች ናቸው ማለት ነው። ሐማ፣ በግዛቱ ውስጥ የሚገኙትን አይሁዳውያን በሙሉ ለማስገደል የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ወደ ንጉሡ ግምጃ ቤት እንደሚያስገባ ተናገረ።d ጠረክሲስም ሐማ ማንኛውንም ትእዛዝ ማውጣትና ትእዛዙን በማኅተም ማጽደቅ እንዲችል የቀለበት ማኅተሙን ሰጠው።—አስ. 3:5-10
-
-
ለአምላክ ሕዝብ ጥብቅና ቆማለችበእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
d ሐማ 10,000 መክሊት ብር ለመስጠት ቃል የገባ ሲሆን ይህ ገንዘብ በዛሬው ጊዜ ባለው የዋጋ ተመን ቢሰላ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ይሆናል። ንጉሡ በእርግጥ ቀዳማዊ ጠረክሲስ ከሆነ ሐማ ያቀረበው ገንዘብ እጅግ አጓጉቶት ሊሆን ይችላል። ጠረክሲስ ለረጅም ጊዜ ሲያቅድ የቆየውን ግሪኮችን የመውጋት ሐሳቡን እውን ለማድረግ ከፍተኛ ገንዘብ ያስፈልገው ነበር፤ ሆኖም ይህ ጦርነት ለከፍተኛ ኪሳራ ዳርጎታል።
-