-
ለአምላክ ሕዝብ ጥብቅና ቆማለችመጠበቂያ ግንብ—2011 | ጥቅምት 1
-
-
ይህ ሁኔታ ሐማን እጅግ አስቆጣው። ይሁንና መርዶክዮስን ማስገደል ብቻ በቂ መስሎ አልታየውም። የመርዶክዮስን ወገኖች በሙሉ ለመደምሰስ ቆርጦ ተነሳ! ሐማ ስለ አይሁዳውያን ለንጉሡ መጥፎ ወሬ በመንገር አሳጣቸው። ምናምንቴ እንደሆኑ በመቁጠር ስማቸውን እንኳ ሳይጠቅስ በሕዝቡ መካከል “ተሠራጭቶና ተበታትኖ የሚኖር አንድ ሕዝብ” እንዳለ ነገረው። ይባስ ብሎም ንጉሡ ያወጣቸውን ሕጎች እንደማያከብሩ ተናገረ፤ ይህም እነዚህ ሰዎች ስጋት የሚፈጥሩ ዓመፀኞች ናቸው የሚል አንድምታ አለው። ሐማ፣ በግዛቱ ውስጥ የሚገኙትን አይሁዳውያን በሙሉ ለማስገደል የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ወደ ንጉሡ ግምጃ ቤት ለማስገባት ሐሳብ አቀረበ።c ጠረክሲስ፣ ሐማ ማንኛውንም ትእዛዝ ማውጣትና ትእዛዙን በማኅተም ማጽደቅ እንዲችል የራሱን የቀለበት ማኅተም ሰጠው።—አስቴር 3:5-10
-
-
ለአምላክ ሕዝብ ጥብቅና ቆማለችመጠበቂያ ግንብ—2011 | ጥቅምት 1
-
-
c ሐማ ቃል የገባው 10,000 መክሊት ብር ለመክፈል ነበር፤ ይህ ገንዘብ በዛሬው ጊዜ ባለው የዋጋ ተመን ቢሰላ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ይሆናል። ንጉሡ በእርግጥ ቀዳማዊ ጠረክሲስ ከሆነ ሐማ ያቀረበው ገንዘብ እጅግ አጓጉቶት ሊሆን ይችላል። ጠረክሲስ ከግሪኮች ጋር ባደረገው አውዳሚ ጦርነት ለከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ተዳርጎ ነበር፤ ይህን ጦርነት ያደረገው አስቴርን ከማግባቱ በፊት ሳይሆን አይቀርም።
-