የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ለአምላክ ሕዝብ ጥብቅና ቆማለች
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • 22. አስቴር ንጉሡ ፊት መቅረብ የፈራችው ለምንድን ነው? (የግርጌ ማስታወሻውንም ተመልከት።)

      22 አስቴር መልእክቱ ሲደርሳት በድንጋጤ ክው ብላ መሆን አለበት። ይህ አጋጣሚ እምነቷን በእጅጉ የሚፈትን ነበር። ለመርዶክዮስ ከላከችው ምላሽ በግልጽ መረዳት እንደሚቻለው አስቴር በጣም ፈርታ ነበር። የንጉሡ ሕግ ምን እንደሚል አስታወሰችው። አንድ ሰው ሳይጠራ ንጉሡ ፊት ቀረበ ማለት ሕይወቱን አጣ ማለት ነው። እንዲህ ዓይነት ጥፋት የፈጸመ ሰው በሕይወት መትረፍ የሚችለው ንጉሡ የወርቅ ዘንጉን ከዘረጋለት ብቻ ነው። አስጢን ንጉሡ ፊት እንድትቀርብ ስትጠራ አሻፈረኝ በማለቷ ከደረሰባት ዕጣ አንጻር አስቴር ንጉሡ ርኅራኄ ያሳየኛል ብላ የምትጠብቅበት ምን ምክንያት ይኖራል? አስቴር ላለፉት 30 ቀናት ንጉሡ ወደ እሱ እንድትገባ እንዳልጠራት ለመርዶክዮስ ነገረችው! አመሉ የማይጨበጠው ይህ ንጉሥ ለረጅም ጊዜ ያልጠራት ከመሆኑ አንጻር በእሱ ዘንድ ያላትን ተወዳጅነት እንዳጣች አድርጋ ብታስብ የሚያስገርም አይሆንም።e—አስ. 4:9-11

  • ለአምላክ ሕዝብ ጥብቅና ቆማለች
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • e ቀዳማዊ ጠረክሲስ ስሜቱ የሚለዋወጥ ግልፍተኛ ሰው በመሆኑ ይታወቃል። ግሪካዊው የታሪክ ምሁር ሄሮዶተስ፣ ጠረክሲስ ከግሪክ ጋር ስላደረገው ጦርነት በጻፈው ታሪክ ላይ ስለ ንጉሡ ባሕርይ የሚገልጹ አንዳንድ ምሳሌዎችን ጠቅሷል። ንጉሡ በሄሌስፖንት ወሽመጥ ላይ መርከቦችን በመደርደር ድልድይ እንዲሠራ ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር። ድልድዩን ማዕበል ባፈረሰው ጊዜ ጠረክሲስ መሃንዲሶቹ አንገታቸው እንዲቀላ ያዘዘ ከመሆኑም ሌላ ከፍ ባለ ድምፅ እርግማን በሚነበብበት ጊዜ አገልጋዮቹ ውኃውን በመግረፍ ሄሌስፖንትን “እንዲቀጡ” መመሪያ ሰጥቷል። ይህ ጦርነት በተካሄደበት ጊዜ አንድ ባለጸጋ ሰው ልጁ ከውትድርና ግዳጅ ነፃ እንዲሆን ሲለምነው ጠረክሲስ ልጁ ለሁለት እንዲቆረጥ ያዘዘ ከመሆኑም ሌላ መቀጣጫ እንዲሆን አስከሬኑ ሌሎች በሚያዩት ስፍራ እንዲቀመጥ አድርጓል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ