-
ለአምላክ ሕዝብ ጥብቅና ቆማለችመጠበቂያ ግንብ—2011 | ጥቅምት 1
-
-
አስቴር መልእክቱ ሲደርሳት በድንጋጤ ክው ብላ መሆን አለበት። ይህ አጋጣሚ እምነቷን በእጅጉ የሚፈትን ነበር። ለመርዶክዮስ ከላከችው ምላሽ መረዳት እንደሚቻለው አስቴር በጣም ፈርታ ነበር። የንጉሡ ሕግ ምን እንደሚል አስታወሰችው። ማንም ሰው ሳይጠራ ንጉሡ ፊት ቀረበ ማለት ሕይወቱን አጣ ማለት ነው። እንዲህ ዓይነት ጥፋት የፈጸመ ሰው በሕይወት መትረፍ የሚችለው ንጉሡ የወርቅ ዘንጉን ከዘረጋለት ብቻ ነው። አስጢን ንጉሡ ፊት እንድትቀርብ ስትጠራ ይህን ለማድረግ አሻፈረኝ በማለቷ ከደረሰባት ዕጣ አንጻር አስቴር ንጉሡ ርኅራኄ ያሳየኛል ብላ የምትጠብቅበት አንዳች ምክንያት ይኖራል? ላለፉት 30 ቀናት ንጉሡ ወደ እሱ እንድትገባ እንዳልጠራት ለመርዶክዮስ ነገረችው! የማይጨበጥ አመል ያለው ይህ ንጉሥ ለረጅም ጊዜ ሳይጠራት የቀረ ከመሆኑ አንጻር በእሱ ዘንድ ያላትን ተወዳጅነት እንዳጣች ብታስብ የሚያስገርም አይሆንም።d—አስቴር 4:9-11
-
-
ለአምላክ ሕዝብ ጥብቅና ቆማለችመጠበቂያ ግንብ—2011 | ጥቅምት 1
-
-
d ቀዳማዊ ጠረክሲስ ስሜቱ በቅጽበት የሚለዋወጥ ግልፍተኛ ሰው በመሆኑ ይታወቃል። ግሪካዊው ታሪክ ጸሐፊ ሄሮዶተስ፣ ጠረክሲስ ከግሪክ ጋር ስላደረገው ጦርነት በጻፈው ታሪክ ላይ ስለ ንጉሡ ባሕርይ የሚገልጹ አንዳንድ ምሳሌዎችን ጠቅሷል። ንጉሡ በሄሌስፖንት ወሽመጥ ላይ ድልድይ እንዲሠራ ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር። ድልድዩን ማዕበል ባፈረሰው ጊዜ ጠረክሲስ መሃንዲሶቹ አንገታቸው እንዲቀላ ያዘዘ ከመሆኑም ሌላ ከፍ ባለ ድምፅ እርግማን በሚታወጅበት ጊዜ አገልጋዮቹ ውኃውን በመግረፍ ሄሌስፖንትን “እንዲቀጡ” መመሪያ ሰጥቷል። ከዚህ ዘመቻ ጋር በተያያዘ ባለጸጋ የሆነ አንድ ሰው ልጁ ከውትድርና ግዳጅ ነፃ እንዲሆን በለመነው ጊዜ ጠረክሲስ ልጁ ለሁለት እንዲቆረጥ ያዘዘ ከመሆኑም ሌላ አስከሬኑን ሌሎች እንዲያዩት በማድረግ መቀጣጫ እንዲሆን አድርጓል።
-