የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 ጥር ገጽ 6-7
  • ከጥር 22-28

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከጥር 22-28
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 ጥር ገጽ 6-7

ከጥር 22-28

ኢዮብ 38–39

መዝሙር 11 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ተፈጥሮን ለመመልከት ጊዜ ትመድባላችሁ?

(10 ደቂቃ)

ይሖዋ ምድርን ከፈጠረ በኋላ ሥራውን መለስ ብሎ ለመመልከት ጊዜ መድቧል (ዘፍ 1:10, 12፤ ኢዮብ 38:5, 6፤ w21.08 9 አን. 7)

መላእክት ጊዜ ወስደው የይሖዋን የፍጥረት ሥራዎች ተመልክተዋል (ኢዮብ 38:7፤ w20.08 14 አን. 2)

ተፈጥሮን ለመመልከትና ለማድነቅ ጊዜ የምንመድብ ከሆነ በይሖዋ ላይ ያለንን እምነት እናጠናክራለን (ኢዮብ 38:32-35፤ w23.03 17 አን. 8)

አንዲት እናትና ትንሽ ልጇ ከቤታቸው ውጭ ሆነው አንዲትን ቢራቢሮ በፈገግታ ሲመለከቱ።

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • ኢዮብ 38:8-10—ይህ ጥቅስ የይሖዋን ሕግ አውጪነት በተመለከተ ምን ያስተምረናል? (it-2 222)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) ኢዮብ 39:1-22 (th ጥናት 5)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(2 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ግለሰቡ የመነጋገር ፍላጎት እንደሌለው ስታስተውል ውይይቱን አዎንታዊ በሆነ መንገድ አቁም። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 3)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(5 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ባለፈው ውይይታችሁ ወቅት ግለሰቡ በቅርቡ የቤተሰቡን አባል በሞት እንዳጣ ነግሮህ ነበር። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 3)

6. ንግግር

(5 ደቂቃ) lmd ተጨማሪ መረጃ ሀ ነጥብ 1—ጭብጥ፦ ዛሬ በዓለም ላይ የሚታዩ ክስተቶችና የሰዎች ባሕርይ መበላሸት ለውጥ እየመጣ እንደሆነ ይጠቁማሉ። (th ጥናት 16)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 111

7. ተፈጥሮን መመልከታችን የእይታ አድማሳችንን እንድናሰፋ ይረዳናል

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ኢዮብ ይሖዋ ስለፈጠራቸው አስገራሚ እንስሳት ሲያሰላስል፤ ከእነሱ መካከል ጉማሬ፣ ራዛ፣ ዝሆን፣ አዞ፣ ንስር፣ ፈረስ እና የዱር በሬ ይገኙበታል። ኃይለኛ ነፋስ እየነፈሰ ነው፤ ኤሊሁ እና ሦስቱ የውሸት አጽናኞች በአቅራቢያው ተቀምጠዋል።

ኢዮብ ከሦስቱ ጓደኞቹና ከሰይጣን ጥቃት ሲሰነዘርበት በደረሰበት ችግርና በተሰነዘረበት ኢፍትሐዊ የሆነ ትችት ላይ ብቻ ማውጠንጠን ጀመረ።

ኢዮብ 37:14⁠ን አንብብ። ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቅ፦

ኢዮብ መንፈሳዊ ሚዛኑን መልሶ ለማግኘት ምን ማድረግ ነበረበት?

የሚደርስብን ፈተና ከአቅማችን በላይ እንደሆነብን ሲሰማን ተፈጥሮን መመልከታችን የይሖዋን ታላቅነት እንድናስታውስ፣ ለእሱ ያለንን ታማኝነት ለመጠበቅ ያለንን ፍላጎት እንድናጠናክር እንዲሁም እሱ እኛን የመንከባከብ ችሎታ እንዳለው ይበልጥ እንድንተማመን ይረዳናል።—ማቴ 6:26

ከኢዮብ መጽሐፍ የምናገኘው ትምህርት—ከእንስሳት የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቅ፦

ይህ ቪዲዮ በይሖዋ ላይ ያላችሁን እምነት ያጠናከረላችሁ እንዴት ነው?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 4 አን. 13-20

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 54 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ