-
ይሖዋ—ኃይሉ እጅግ ታላቅ ነውመጠበቂያ ግንብ—2000 | መጋቢት 1
-
-
5. የይሖዋ ብርታት በሥራዎቹ ላይ ተንጸባርቆ የምናየው እንዴት ነው?
5 እኛም እንደ ዳዊት ‘የአምላክን ሥራዎች ብንፈልግ’ በነፋሱና በሞገዱ፣ በነጎድጓዱና በመብረቁ፣ በሚያስገመግሙት ወንዞችና ግዙፍ በሆኑት ተራራዎች ላይ የተንጸባረቀውን ኃይሉን መመልከት እንችላለን። (መዝሙር 111:2፤ ኢዮብ 26:12-14) ከዚህም በላይ ይሖዋ ኢዮብን እንዳሳሰበው እንስሳትም ቢሆኑ የእርሱን ኃይል ይገልጣሉ። ከእነዚህ መካከል አንዱ ቤህሞት ወይም ጉማሬ ነው። ይሖዋ ኢዮብን “እነሆ፣ ብርታቱ በወገቡ ውስጥ ነው፤ . . . አጥንቱ እንደ ናስ አገዳ ነው” ብሎታል። (ኢዮብ 40:15-18) በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ያልተገራ በሬ ያለው አስፈሪ ኃይልም በሰፊው የታወቀ ነበር። ዳዊት ‘ከአንበሳ አፍና ከዱር በሬ ቀንድ አድነኝ’ ሲል ጸልዮአል።—መዝሙር 22:21 NW ፤ ኢዮብ 39:9-11
6. በሬ በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ምን ያመለክታል? ለምንስ? (የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት።)
6 በሬ ካለው ጥንካሬ የተነሣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የይሖዋን ኃይል ለማመልከት ተሠርቶበታል።c ሐዋርያው ዮሐንስ ስለ ይሖዋ ዙፋን የተመለከተው ራእይ አራት ሕያዋን ፍጥረታት የታዩበት ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንዱ እንደ በሬ ያለ መልክ ነበረው። (ራእይ 4:6, 7) በዚህ ኪሩብ የተወከለው ከይሖዋ አራት ዋና ዋና ባሕርያት አንዱ ኃይል እንደሆነ በግልጽ መረዳት ይቻላል። ሌሎቹ ፍቅር፣ ጥበብና ፍትሕ ናቸው። ኃይል በአምላክ ስብዕና ውስጥ ይህን ያህል ጎላ ያለ ስፍራ ያለው በመሆኑ ስለ ኃይሉና ይህን ኃይሉን እንዴት እንደሚጠቀምበት የጠራ ግንዛቤ ማግኘታችን ወደ እርሱ እንድንቀርብና ያለንን ማንኛውንም ኃይል በአግባቡ በመጠቀም ረገድ የእርሱን ምሳሌ እንድንኮርጅ ይረዳናል።—ኤፌሶን 5:1
-
-
ይሖዋ—ኃይሉ እጅግ ታላቅ ነውመጠበቂያ ግንብ—2000 | መጋቢት 1
-
-
c በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሠራበት በሬ የሚለው ቃል (በላቲን ዩረስ ) አዉራከስ የሚለው እንደሆነ ግልጽ ነው። ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት እነዚህ እንስሳት በጋውል (በዛሬዋ ፈረንሳይ) ይገኙ የነበረ ሲሆን ጁሊየስ ቄሣር እነርሱን በተመለከተ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “እነዚህ ዩራይ ከዝሆን የማይተናነሱ ሲሆን ተፈጥሯቸው፣ ቀለማቸውና መልካቸው ግን የበሬ ነው። ያላቸው ጉልበትም ሆነ ፍጥነታቸው እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ዓይናቸው የገባውን ሁሉ ሰውም ሆነ እንስሳ አይምሩም።”
-