የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በሕይወትህ ውስጥ ከሁሉ የላቀውን ቦታ የምትሰጠው ለማን ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | ግንቦት 15
    • 7, 8. ኢዮብ ምን ዓይነት መከራዎች አጋጥመውታል? በታማኝነት በመጽናቱ ምን አሳይቷል?

      7 ሰይጣን በኢዮብ ላይ ተደራራቢ መከራዎችን እንዲያመጣበት ይሖዋ ፈቀደ። (ኢዮብ 1:12-19) ኢዮብ ሰይጣን ባመጣበት መከራ የተነሳ ሰማይ ምድሩ ሲገለባበጥበት ምን አደረገ? መጽሐፍ ቅዱስ “ኢዮብ አልበደለም፤ በእግዚአብሔርም ላይ ክፉ አልተናገረም” በማለት መልሱን ይሰጠናል። (ኢዮብ 1:22) ሰይጣን ግን መሸነፉን አምኖ አልተቀበለም። “‘ቍርበት ስለ ቍርበት ነው’ እንዲሉ ሰው ለሕይወቱ ሲል ያለውን ሁሉ ይሰጣል”b የሚል ሌላ ተቃውሞ አሰማ። (ኢዮብ 2:4) ኢዮብ በአካሉ ላይ መከራ ቢደርስበት በሕይወቱ ውስጥ ከሁሉ የላቀውን ቦታ ለይሖዋ መስጠቱን እንደሚተው ሰይጣን ተናገረ።

  • በሕይወትህ ውስጥ ከሁሉ የላቀውን ቦታ የምትሰጠው ለማን ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | ግንቦት 15
    • b አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑራን “ቍርበት ስለ ቍርበት ነው” የሚለው አገላለጽ ኢዮብ የራሱ ቍርበት ወይም ሕይወት እስካልተነካ ድረስ የልጆቹና የእንስሶቹ ቁርበት ወይም ሕይወት ቢያልፍ ምንም እንደማይመስለው የሚያመለክት ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ። ሌሎች ደግሞ ይህ አነጋገር፣ አንድ ሰው ሕይወቱን ለማዳን ሲል ከቍርበቱ የተወሰነውን ለማጣት ፈቃደኛ ሊሆን እንደሚችል የሚያጎላ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ለምሳሌ ያህል፣ አንድ ሰው ጭንቅላቱ እንዳይመታ በእጁ ሊመክት በሌላ አባባል ቍርበቱን ወይም ሕይወቱን ለማትረፍ ሲል ከቍርበቱ የተወሰነውን ለማጣት ፈቃደኛ ሊሆን ይችላል። ይህ ምሳሌያዊ አነጋገር ትርጉሙ ምንም ይሁን ምን፣ ኢዮብ ሕይወቱን ለማትረፍ ሲል ማንኛውንም ነገር መሥዋዕት ለማድረግ ፈቃደኛ እንደሚሆን የሚጠቁም መሆኑ ግልጽ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ