የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 1/1 ገጽ 32
  • “በሰማያት ያለችው የታመነች ምስክር”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “በሰማያት ያለችው የታመነች ምስክር”
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 1/1 ገጽ 32

“በሰማያት ያለችው የታመነች ምስክር”

የመጀመሪያው ሰው በምድር ላይ መኖር ከመጀመሩ ከረዥም ጊዜ አስቀድሞ ጨረቃ በምሽት ሰማይ ላይ ሆና ብሩሕ ብርሃኗን ትሰጥ ነበር። ባንድ ወቅት ደግሞ ብዙ ሰዎች እንደ እንስት አምላክ አድርገው አምልከዋታል። ፕሉታርክ የተባለው ግሪካዊ ደራሲ ጨረቃ ንጹሐን ነፍሳት ከሞት በኋላ በመጨረሻው የሚሄዱባት ሥፍራ ናት ብሎ ተናግሯል። በቦልቲክ አፈ ታሪክ ጨረቃ ፀሐይን ትቶ በመሄዱ በሰማይ ላይ አብረው የሚታዩት አልፎ አልፎ ብቻ ሆነ ብሎ ይህ አፈ ታሪክ ይናገራል።

ወጣት የሆኑና ከወጣትነት ዕድሜ ያለፉ ፍቅረኛሞች በአሁኑ ጊዜ ጨረቃን አሻቅበው እየተመለከቱ የፍቅርን ነገር ያስባሉ። በ1960ዎቹ ውስጥ የሳይንስ ሊቃውንት ሰዎችን ወደ ጨረቃ ለመላክና ለምርምር የሚሆን ጥቂት ፓውንድ ኮረት እንዲያመጡ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ አውጥተዋል። ስለጨረቃ እርግጠኛ የሆነ አንድ ነገር አለ። እርሱም በየቀኑ በተመደበላት ጊዜ የምትወጣና የምትገባ መሆኗ ነው። በተመደበላት መዞርያዋ በመዞር በጣም የታመነች ከመሆኗ የተነሳ ባለፉት ሺህ ዓመታት በፊት ውስጥ ያለፈችባቸው መልኮቿና ግርዶሾቿ ሁሉ በስሌት ሊደረስባቸው ይቻላል።

እሥራኤላውያን ጨረቃን ሲመለከቱ አንድ አስደናቂ ነገር ትዝ ይላቸው ነበር። አምላክ ለንጉሥ ዳዊት ንጉሣዊ ሥርወ መንግሥቱ እንደማያልፍ ቃል ገብቶለት ነበር። “[የዳዊት ዘር] በሰማይ በእውነተኛነት እንደምትመሰክረው እንደ ጨረቃ የጸና ይሆናል” ብሏል። (መዝሙር 89:35-37) እንደ 1980 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም) ይህ ትንቢት “የዳዊት ልጅ” በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ተፈጽሞአል። (ሉቃስ 18:38) ኢየሱስ ከሞተ በኋላ ከሙታን ተነስቶ የማይሞት መንፈሳዊ አካል በመሆን ወደ ሰማይ አርጓል። (ሥራ 2:34-36) እርሱም ከጊዜ በኋላ የአምላክ ሰማያዊት መንግሥት ንጉሥ ሆኖ ተሾሞአል። (ራእ 12:10) ያች መንግሥት አሁን በመግዛት ላይ ያለች ስትሆን “ለዘላለም [ጸንታ] ትቆማለች።” (ዳንኤል 2:44) በዚህም መንገድ የማይሞተው የዳዊት ንጉሣዊ ሥርወ መንግሥት ወኪል የሆነው ኢየሱስ “በሰማይ ያለችው የታመነች ምስክር” የሆነችው ጨረቃ እስካለች ድረስ ይኖራል።

ስለዚህ ጨረቃ በምሽት ሰማይ ላይ ደምቃ ስታበራ በምትመለከትበት ጊዜ አምላክ ለዳዊት የሰጠውን ተስፋ አስታውስና የአምላክ መንግሥት ለአምላክ ክብርና ለታማኞቹ የሰው ልጆች ዘላለማዊ በረከት ለማምጣት አሁን በመግዛት ላይ በመሆኗና ለወደፊቱም ለዘላለም የምትገዛ በመሆኗ ምስጋና አቅርብ።—ራእይ 11:15

[ምንጭ]

Frank Zullo

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ