-
በትንቢት እንደተነገረው ሁሉን አዲስ ማድረግመጠበቂያ ግንብ—2000 | ሚያዝያ 15
-
-
10. ኢሳይያስ የተነበየውን “አዲስ ምድር” ልንረዳው የሚገባው እንዴት ነው?
10 “ምድር” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁልጊዜ ግዑዟን ምድር ብቻ አያመለክትም። ለምሳሌ ያህል መዝሙር 96:1 ቃል በቃል “ምድር ሁሉ፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ” ይላል። የምንኖርባት ፕላኔታችን ማለትም ደረቁ ምድርም ሆነ ሰፊው ውቅያኖስ ሊዘምሩ እንደማይችሉ እናውቃለን። ሰዎች ግን ይዘምራሉ። አዎን፣ መዝሙር 96:1 የሚናገረው በምድር ላይ ስለሚኖሩ ሰዎች ነው።a ይሁን እንጂ ኢሳይያስ 65:17 ስለ ‘አዲስ ሰማይም’ ይናገራል። ‘አዲሱ ምድር’ ወደ ትውልድ አገራቸው የተመለሱትን አዲስ የአይሁድ ኅብረተሰብ ካመለከተ “አዲስ ሰማይ” የሚለውስ መግለጫ ምን ያመለክታል?
-
-
በትንቢት እንደተነገረው ሁሉን አዲስ ማድረግመጠበቂያ ግንብ—2000 | ሚያዝያ 15
-
-
a ዘ ኒው ኢንግሊሽ ባይብል መዝሙር 96:1ን “በምድር ላይ የምትኖሩ ሰዎች ሁሉ ለጌታ ዘምሩ” ሲል ተርጉሞታል። ዘ ኮንተምፕረሪ ኢንግሊሽ ቨርሽን ደግሞ “በዚህ ምድር ላይ የምትኖሩ ሁሉ ለጌታ ውዳሴ ዘምሩ” ይላል። ይህ አባባል ኢሳይያስ ወደ አገራቸው የተመለሱትን የአምላክ ሕዝቦች ለማመልከት “አዲስ ምድር” ብሎ ከተናገረው ጋር የሚስማማ ነው።
-