የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ጥበብን የሚያገኝ ሰው ደስተኛ ነው”
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | መጋቢት 15
    • “ትጮሃለች”

      ምሳሌ ምዕራፍ 8 “በውኑ ጥበብ አትጮኽምን? ማስተዋልስ ድምፅዋን አትሰጥምን?” የሚሉ መልስ የማ​ያሻቸውን ጥያቄዎች በማንሳት ይጀምራል።a አዎን፣ ጥበብና ማስተዋል ያለማቋረጥ ይጮኻሉ፤ ሆኖም የሚያሰሙት ድምፅ ጨለምለም ባሉ ቦታዎች ላይ አድብታ ብቻውን ሲንቀዋለል ለምታገኘው ተሞክሮ የሌለው ወጣት ሸንጋይ ቃላቶችን ሹክ ከምትል ሥነ ምግባር የጎደላት ሴት የተለየ ነው። (ምሳሌ 7:​12) “በኮረብታ ላይ በመንገድ አጠገብ በጎዳና መካከል ትቆማለች። በበሩ አጠገብ በከተማይቱም መግቢያ፣ በደጁ መግቢያ ትጮኻለች።” (ምሳሌ 8:​1-3) ጥበብ የምታሰማው ድምፅ በየአደባባዩ ማለትም በበሩ አጠገብ፣ በጎዳና መካከል እንዲሁም በከተማው መግቢያ ጎልቶና ጥርት ብሎ ይሰማል። ሰዎች ያለ አንዳች ችግር ሰምተው ምላሽ መስጠት ይችላሉ።

      በመንፈስ አነሳሽነት በተጻፈውና የአምላክ ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኘውን አምላካዊ ጥበብ የፈለገ ማንኛውም ሰው በቀላሉ ሊያገኘው እንደሚችል ማን ሊክድ ይችላል? ዘ ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፔድያ “በታሪክ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል በብዙዎች ዘንድ የሚነበብ መጽሐፍ የለም” ብሏል። አክሎም “የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል በሰፊው የተሠራጨ መጽሐፍ አይገኝም። ከዚህም በላይ የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል ብዙ ጊዜና በብዙ ቋንቋዎች የተተረጎመ መጽሐፍ የለም” ብሏል። ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ከ2, 100 በሚበልጡ ቋንቋዎችና ቀበሌኛዎች የተተረጎመ ሲሆን ከዓለም ሕዝቦች መካከል ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ቢያንስ የአምላክን ቃል የተወሰነ ክፍል በገዛ ቋንቋቸው ለማንበብ ይችላሉ።

      የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስ የያዘውን መልእክት በየሥፍራው ለሕዝብ በማወጅ ላይ ናቸው። የአምላክን መንግሥት ምሥራች 235 በሚያክሉ አገሮች ውስጥ በትጋት ይሰብካሉ እንዲሁም በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘውን እውነት ለሰዎች ያስተምራሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱት ሁለቱ መጽሔቶቻቸው ማለትም በ140 ቋንቋዎች የሚታተመው መጠበቂያ ግንብ እና በ83 ቋንቋዎች የሚታተመው ንቁ! መጽሔት እያንዳንዳቸው ከ20 ሚልዮን በሚበልጡ ቅጂዎች ይሰራጫሉ። በእርግጥም፣ ጥበብ በየአደባባዩ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ ትጮሃለች!

  • “ጥበብን የሚያገኝ ሰው ደስተኛ ነው”
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | መጋቢት 15
    • a “ጥበብን” ለመግለጽ የገባው የዕብራይስጥ ቃል አንስታይ ጾታን የሚያመለክት ስለሆነ አንዳንድ ትርጉሞች ጥበብን በሚጠቅሱበት ጊዜ የአንስታይ ጾታ ተውላጠ ስም ይጠቀማሉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ